1793196926375

የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር በቀጣይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሊያደርግባቸው ካቀደባቸው ቋንቋዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አንዱ የሆነውን የዶርዜ ቋንቋ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሥራን ለመጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።

​ማኅበሩ ባወጣው መረጃ እንዳመለከተው ባለፉት በርካታ ወራት ይህንኑ የትርጉም ሥራ ለማስጀመር የሚያስችሉ ሰፊ ጥናቶችንና የፕሮጀክት ቀረጻዎችን ያደረገ ሲሆን በዞኑ ካሉ አብያተ ክርስቲያናትና ልዩ ልዩ የማኅበረሰቡ ክፍሎች ጋርም ፍሬያማ ውይይቶችን ማድረጉን ይፋ አድርጓል።

​ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለትርጉም ሥራው ስኬት አስፈላጊ የሆኑ ​ኮምፒዩተሮችን፣ ​ልዩ ልዩ መጻሕፍትን እና ​የቢሮ ቁሳቁሶችን የማዘጋጀት ሥራዎችን ሙሉ በሙሉ አጠናቋል።

​በአሁኑ ወቅት የዝግጅቱ የመጨረሻ ምዕራፍ የሆነው የተርጓሚዎች ስልጠና ከተጠናቀቀ በኋላ በቀጣይ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ የትርጉም ሥራው በይፋ እንደሚጀመርም አስታውቋል።

የትርጉም ሥራው ዋና ጽሕፈት ቤትም በአርባ ምንጭ ከተማ እንዲሆን መወሰኑ ተገልጿል።

​የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር የእግዚአብሔር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ በሁሉም የሀገራችን ቋንቋዎች እንዲተረጎምና እንዲታተም የሚያደርገውን ጥረት በማጠናከር ላይ የሚገኝ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በ14 ልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝም ባወጣው መረጃ ጠቁሟል።

​Voice of Marginalized Community – WT Media