የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለአሜሪካው ፕረዚዳንት ዶኖልድ ትራምፕ ዛቻ ምላሽ ሰጡ

“ሰውየው የሚያወራውን አያውቅም፣ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን በእንዲህ አይነት ሀላፊነት የጎደለው አነጋገር ፍርሀት አይገባቸውም፣ ታሪክ ሁሉንም ያስተምራል”— የቀድሞው ጠ/ሚር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በስፒከርፎን አማካኝነት ከእስራኤል እና ሱዳን መሪዎች ጋር በመሆን አዲስ በተደረሰው የሰላም ስምምነት ዙርያ ጋዜጣዊ መግለጫ በተሰጠበት ወቅት ስለ ህዳሴው ግድብ – “ግድቡ ወደ ግብጽ የሚፈሰውን ውሃ ያቆማል”

  • “ኢትዮጵያ ያዘጋጀነውን ስምምነት ጥሳለች ይህ ጥሩ አይደለም ያንን ማድረግ አይችሉም ያንን ማድረግ ይችላሉ ብዬ አላስብም”
  • “በዚህ ምክንያት ብዙ ገንዘብ ከኢትዮጵያ ቆርጠናል በውሉ ካልተስማሙ በስተቀር ያንን ገንዘብ ደግመው አያዩትም”
  • “ከሱዳን ጋርም በዚህ ጉዳይ ተነጋግሪያለው”
  • “ያለው ሁኔታ አደገኛ ነው፣ ግብፆች በዚህ ሁኔታ ሊኖሩ አይችሉም፣ ግድቡን ያፈነዱታል” ፕሬዝዳንቱ ማለታቸውን ተከትሎ ነው።

Its#our#Dam🇪🇹🇪🇹🇪🇹