የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎበኙ።
የሃይማኖት አባቶቹ የዘመን መለወጫን ምክንያት በማድረግ ቡራኬ ለመስጠትና የግድቡን ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት አስመልክቶ ስሜትና አጋርነታቸውን ለመግለፅ ወደሥፍራው ተጉዘዋል።
ጉብኝቱ በሠላም ሚኒስቴርና በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን የጉባኤው የበላይ ጠባቂ አባቶችና ተወካዮቻች ተሳትፈውበታል።
በጉብኝቱ ወቅት የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ በሰጡት ማብራሪያ ግድቡ በጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር መግለፃቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
