የአሜሪካው ታዋቂው ታይም መጽሔት የ2021 የዓለማችን 100 ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን አንባቢዎቹ እንዲመርጡለት ባወጣው ዝርዝር ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን አካቷል፡፡
በፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ፣ በኪነጥበብ፣ በስፖርት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ በአመራር እንዲሁም በሌሎችም ዘርፎች በተያዘው የአውሮፓዊያኑ 2021 በዓለማችን ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳረፉ ግለሰቦችን ነው አንባቢዎቹ እንዲመርጡለት መፅሔቱ ያቀረበው፡፡
ታይም ካቀረባቸው በርካታ ዕጩ ተመራጮች ውስጥ 18 የዓለማችን መሪዎች በተካተቱበት ዝርዝር ውስጥ ከአፍሪካ ሁለት መሪዎች 100 ተጽዕኖ ፈጣሪ ምርጦች ውስጥ ለመግባት በዕጩነት ቀርበዋል፡፡
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የታይምን ትኩረት የሳቡ መሪዎች ሆነው ነው ከአፍሪካ ለምርጫው የቀረቡት፡፡
የአሜሪካ፣እንግሊዝ፣ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ቱርክ፣ሩሲያና ቻይና መሪዎችም በታይም መፅሄት ለምርጫ ከቀረቡት 19 የዓለም መሪዎች ውስጥ ተካተዋል፡፡
የታይም መፅሔት ከአምስት ቀናት በኃላ የአንባቢዎቹን ከፍተኛ ድምፅ ያገኙ ግለ ሰብዕናዎች የዓለማችን የዓመቱ 100 ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዝርዝር ውስጥ አካቶ አሸናፊዎቹን ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
መራጮች በኦንላይን የቀረበላቸው ማስፈንጠሪያ በመከተል እና የኢሜል አድራሻቸውን በማስገባት “Yes” ወይም “No” ከሚሉ ሁለት አማራጮች አንዱን በመንካት በተለያዩ ዘርፎች ከቀረቡ ዕጩዎች የሚፈልጉትን ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰብ መምረጥ ይችላሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በታይም መፅሔት 100 ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ዝርዝር ውስጥ ለመግባት ለምርጫ የቀረቡበት ማስፈንጠሪያ የሚከተለው ነው፡፡
https://time.com/time-100-reader-poll-2021/
