በበዓሉ የሠላም አምባሳደር የሆኑት የጋሞ ሐገር ሽማግሌዎች ፈጣሪ ለሀገራችን አንድነት፣ ፍቅርን፣ ሠላምንና ብልፅግናን ተመኝተዋል፡፡
እንደ ዞኑ መንግስት ጉዳዮች መምሪያ ዘገባ የጋሞ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ በዓሉ የዞናችን ህዝቦች የአብሮነት እና የአንድነት ማሳያ ከመሆኑ ባሻገር የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ ነው ብለዋል፡፡
” ማስቃላ” በዓል የደስታ፣ የፍቅርና የፍሰሐ በዓል መሆኑን የገለፁት አቶ ብርሃኑ ወቅቱ የህልዉና ዘመቻ እየተካሄ ያለበት በመሆኑ የዞኑ ነዋሪዎች ያላቸውን ከዘማች ቤተሰቦች ጋር በመካፈል እንዲያከብሩ አሳስበዋል፡፡


