በኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም የሶዶ ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ አቶ ተመስገን ያይና ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት እንደገለጹት ተቋሙ ላለፉት 24 ዓመታት ብዙ ውጣ ውረዶችን በማለፍ የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን አንጋፋው ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አሁን ደግሞ ኦሞ ባንክ አክሲዮን ማህበር እንዲሆን ሊወሰን የቻለው የተቋሙ አመራሮች፣ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎች የተቋሙ ባለድርሻ አካላት፣ ደንበኞችና መላው የህብረተሰብ ክፍሎች ባደረጋችሁት ጠንካራ ድጋፍ በመሆኑ በስኬቱ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
በዲስትሪክቱ ስር ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች ተቋሙ በቁጠባ አሰባሰብ፣ በብድር ስርጭት እና በዕዳ አመላለስ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የሰሩት ጠንካራ ስራ ለዚህ ውጤት ከፍተኛ ድርሻ የሚይዝ በመሆኑ ለትጋታችሁ ትልቅ እውቅና ይሰጣል ብለዋል አቶ ተመስገን።
ሁሉም ባለሙያዎች ዘመኑ የውድድር በመሆኑ ከዘመኑ ጋር አብሮ መዘመን የሚችል ቅልጥፎናና ትጋት በመላበስ ባንኩን በተሻለ ስኬት ለመምራትና የደንበኞችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከወዲሁ ሙሉ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
ተቋሙ ወደ ባንክ ደረጃ በማደጉ ለአካባቢው ህብረተሰብ የሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍቸኛ በመሆኑ መላው ህብረተሰብ የተለመደውን አጋሪነት አጠናክሮ በመቀጠል ተጠቃሚነቱን ከፍ እንዲያደርግ ስራ አስኪያጁ ጥሪ አቅርበዋል።
