🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
➡ ውድ የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የዎላይታ ዞን ነዋሪዎች!!
➡ ውድ የተወደዳችሁ በውጭ ሀገርም ሆነ በሀገር ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የምትኖሩ የወላይታ ብሔር ተወላጆች!!
➡ ውድ የተወደዳችሁ መላው የሀገራችን ህዝቦች!!
እንኳን ለ2⃣0⃣1⃣4⃣ ዓ/ም የዎላይታ ብሄር የዘመን መለወጫ ግፋታ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ፤ አደርሰን በማለት በራሴና በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስም መልካም ምኞቴን ሳበስራችሁ ላቅ ያለ ደስታ እተሰማኝ ነው፡፡
እንኳን ለ2⃣0⃣1⃣4⃣ዓ.ም የዎላይታ አዲስ ዓመት ግፋታ በዓል በሠላም፣ በደስታ፣ በፍቅር አደረሳችሁ፣አደረሰን!!
🌻ዮዮ ግፋታ🌻
ግፋታ በዎላይታ ብሔር ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበር እና ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የዎላይታ ብሔር የማንነት መገለጫ ፤ የአሮጌ ዓመት ማብቂያ እና የአዲሱ ዓመት ማብሰሪያ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በሌላ መልኩ ደግሞ በዎላይታ ብሔር ዘንድ ግፋታ “መሻገር” ማለት ሲሆን፤ ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ፤ ከጥላቻ ወደ እርቅ፤ ከመጥፎ ሥራ ወደ ጥሩ ስራ የምንሻገርበትን ቃል ጭምር የሚያመላክት “በኩር ወር” ነውና እኛም የ2⃣0⃣1⃣4⃣ ዓ.ም የግፋታን በዓል ስናከብር በታላቅ ወንድማማችነት፣ በመተሳሰብ፣ በመደጋገፍ፣ በመቻቻል፣ በአብሮነት፣ ይቅር በመባባል እንዲሁም ስለ ሠላም ስንል እጅ ለእጅ ተያይዘን በአብሮነት በዓሉን የምናሳልፍበት እንዲሆን ጭምር መልካም ምኞቴን ልገልጽላችሁ እወዳለሁ፡፡
ውድ የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የዎላይታ ዞን ነዋሪዎች፤ ውድ የተወደዳችሁ በውጭ ሀገርም ሆነ በሀገር ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የምትኖሩ የዎላይታ ብሔር ተወላጆች እንዲሁም ውድ የተወደዳችሁ መላው የሀገራችን ህዝቦች!!
የ2⃣0⃣1⃣4⃣ዓ.ም የግፋታ በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና፣ የደስታ የብልጽግና እንዲሆንልን ጭምር አሁንም በራሴና በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስም መልካም ምኞቴን ደግሜ ደጋግሜ ልገልጽላችሁ እወዳለሁኝ፡፡
🌻ዮዮ ግፋታ🌻
ግፋታ በርካታ ባህላዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያው እና ስነ ልቦናዊ ፋይዳዎችን በውስጡ የያዘ ታላቅ በዓል እንደ መሆኑ መጠን በዓለም አቀፍ ደረጃ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ በዩኒስኮ እንዲመዘገብ እና ባሕላዊ ትውፊቱ የበለጠ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገር የዩኒቨርሲቲያችን የዘርፉ ተመራማሪዎች በጥናትና ምርምር ላደረጉትና አሁንም እያደረጉ ላሉት ዘርፈ ብዙ እገዛ በዚሁ አጋጣሚ በሠፊው ሕዝብ ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁኝ፡፡
ዩኒቨርሲቲያችንም ባለፉት ጥቂት ዓመታት የግፋታ በዓል ታሪካዊ ዳራን አስመልክቶ ሰፋ ያለ ጥናትና ምርምር በማካሄድ፣ በሀገር አቀፍ ታዋቂ በሆኑ መገናኛ ብዙሃን ዘጋቢ ፊልም በማሰራት፣ በዘርፉ የተሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች በሕትመት ውጤቶች በማሳተም ብሎም ለጥናትና ምርምር ስራ አስፈላጊውን ሀብት በመመደብ መጠነ ሰፊ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ የተሻለ ውጤትም ታይቶበታል።
ቀጥሎ ባሉ ጊዜያትም ግፋታ በአለም ደረጃ በዩኔስኮ በማይዳሰሱ ቅርሶች ለማስመዝገብ እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ ዩኒቨርሱቲው ከዎላይታ ህዝብ እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀቶ አበክሮ እንደሚሰራ ፤ ለዚሁም የተጀመረውን የጥናትና ምርምር ስራ አጠናክሮ በማስቀጠልም ሆነ አስፈላጊውን ሀብት በመመደብ ጭምር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ላበስርላችሁ እወዳለሁኝ፡፡
ዓለም አቀፍ ወርርሽኝ የሆነው ኮቪድ-19 አሁንም ቢሆን እየጨመሩ ስለመጣ ራሳችንን ሆነ መላውን ወገኖቻችንን ከኮሮና በሽታ እየተከላከልንና ባለን ነገር ሁሉ በኢኮኖሚ አቅመ ደካማ የሆኑ ግለሰቦችን በመርዳት፤ በፍጹም ወንድማማችነት ካለን ላይ በማካፈል በኢትዮጵያዊነት መተሳሰብ የግፋታን በዓል እንድናከብር አሁንም ደግሜ ወንድማዊ ጥሪዬን እያቀረብኩ፤ በዓሉ የሠላም፣የፍቅር፣ የደስታ እንዲሁም የብልጽግና እንዲሆንላቹ እመኛለሁ፡፡
🌻መልካም የግፋታ በዓል!🌻
🌻ዮዮ ግፋታ🌻
➡ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!!
ፕ/ር ታከለ ታደሰ-የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት
አመሰግናለሁ!!🖤💛❤️