ግልጽነትና ተዓማኒነት የታየበት ታሪካዊው ምርጫ በወርሃ ሰኔ ላይ በተከናወነበት ወቅት በልዩ ልዩ ምክንያቶች ምርጫውን በወቅቱ ማከናወን ያልቻሉ ወገኖቻችን፣ ምርጫ ቦርድ በያዘው ተለዋጭ ቀጠሮ መሰረት ዛሬ ዴሞክራሲያችንን ምሉእ የሚያደርገውን ምርጫ መከናወኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናግረዋል።
ምንም አይነት የጸጥታ ችግር ሳያጋጥም፣ ድምጻቸውን ይበጀኛል ለሚሉት የፖለቲካ እጩ በመስጠት የዜግነት ግዴታቸውን በድል መወጣታቸውን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚኖሩ የኮንታ፣ የምዕራብ ኦሞ፣ የቤንች ሸኮ፣ የከፋ፣ የዳውሮና የሸካ ሕዝቦች መተዳደር የሚፈልጉበትን የአስተዳደር ክልል በሕዝበ ውሳኔአቸው ማሳወቃቸውንም አጋርተዋል። ሁለቱም የዴሞክራሲ ሂደቶች ላይ በነጻነት ፍላጎታቸውን በድምጻቸው መፈጸም ለቻሉ ዜጎቻችንን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል።
እነዚህ ሰላማዊ የሆኑ የዴሞክራሲ ልምምዶች በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወን ምርጫ በማስፈጸም ሂደት ውስጥ የተካፈላችሁ አካላት በሙሉ፣ በወንድማማችነት እሴት ላይ ኢትዮጵያዊ መልክ ይዞ እየተገነባ ለሚገኘው ሕብረ ብሔራዊ የዴሞክራሲ ሥርዓታችን መዳበር አሻራችሁን አኑራችኋልና ኢትዮጵያ ታማሰግናችኋለች በማለትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ሚዲያ ገልፀዋል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡Wolaita Timese/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw…
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
#WolaitaTimes, 20/01/14 E.C , Sodo, #Ethiopia🇪🇹
