ከተለያዩ የአለም ሀገራት የተውጣጡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች በኢትዮጵያ አየር ኃይል ጉብኝት አደረጉ፡፡
በአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ሐረር ሜዳ ዙሪያ ያሉ ክፍሎችንና በተቋሙ ውስጥ የተሰሩ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን የጎበኙት ዲያስፖራዎቹ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሁለንተናዊ መልኩ ተቋማዊ አደረጃጀቱን በማዘመን በከፍተኛ የለውጥ ጉዞ ላይ መገኘቱን ከጉብኝቱ መታዘባቸውን ጠቅሰው በዚህ ውጤታማ ተግባር ትልቅ ኩራት የተሰማቸው መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለአየር ሎጂስቲክስ ብ/ጀነራል ነገራ ሌሊሳ በበኩላቸው ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ትልቅ ስምና ዝና ያለው አንጋፋ የአቪየሽን ተቋም መሆኑን አዉስተው ፣ በተለይም ከለውጡ ወዲህ በተቋማዊ ሪፎርም የግዳጅ አፈፃፀሙን ይበልጥ በማሳደግ በ2022 በአፍሪካ ቀዳሚ ተመራጭ የአቪየሽን ተቋም ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
በዕለቱ በአየር ኃይል ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል መሠረት ጌታቸው አማካኝነት ስለተቋሙ አጠቃላይ ሁኔታ ሰፊ ማብራሪያና ገለፃ ተደርጓል።
በፍቅሬ በቀለ – የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት