
ትምህርት ቤት ማለት የሰው ልጆች የአስተሳሰብ ደረጃን ከፍ ለማድረግና በሁሉም እይታ ወደፊት እንዲጓዝ መሠረት የሚጣልበት መነሻ ቦታ ነው በማለት የደቡብ ክልል ም/ር/መስተዳድር እና የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ተስፋዬ ይገዙ በምረቃ ወቅት ተገኝተው ተናግረዋል።
በአስተሳሰብና በአመለካከት የተሻሉና ለሀገር እድገት ግብዓት የሚሆኑ ምሁራን እንዲበረከቱ ለማድረግ ለተማሪዎች፣ ለመምህራንና ለወላጆች ምቹ የሆነ ት/ቤት መፈጠር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
ልጆች በጥሩ ስነምግባርና በዕውቀት የላቁ ሆኖ እንድወጡ የመምህራንና የወላጆች ሚና ከፍተኛ መሆኑን አቶ ተስፋዬ ገልጸው ት/ቤት ህብረተሰቡ እንደ ራሱ ንብረት በመጠበቅ፣ ውብና ፅዱ በማድረግ፣ የልጆቻቸውን ት/ት ሁኔታ በመከታተልና ለት/ቤቱ እድገት የበኩላቸውን ምና መጫወት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የአከባቢው ማህበረሰብ በቀጣይ የተሻለ ልማት ለማግኘት ዛሬ በእጃችን ላይ የገባውን በሚገባ መጠበቅ ተገቢ ነው ያሉት አቶ ተስፋዬ ትምህርት ቤቱን ሞደል ለማድረግ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
ይህ የበቅሎ ሰኞ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ስገነባ ለሚቀጥሉት 100 ዓመታት ያለ ምንም ችግር አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ የተገነባ ስሆን በቃጣይ ህዳር ወር መጀመሪያ ላይ የምረቃ ስነ-ስርዓት ይከናወናል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዞኑ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ዛሬ በተደረገው የርክክብ ስነ ስርዓት ላይ ከክልልና ከዞን የተጋበዙ ክቡር እንግዶች የተገኙ ስሆን ህብረተሰብ በአጠቃላይ ት/ቤቱን እንደ ግል ንብረት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፈዋል።