• አቶ አክሊሉ ለማ የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳደሪ በመሆን ተሾሙ 

አቶ አክሊሉ ለማ የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው እስከተሾሙ ድረስ የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ቢሮ ኃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ ነበር።

በጉተራ አዳራሽ እየተካሄደ በሚገኘው የዞኑ 4ኛ ዙር 9ኛ የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ምክርቤት ጉባኤ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙ አቶ አክሊሉ ለማ ጨምረው ወይዘሮ ካሰች ኤሊያስ የምክርቤቱ ዋና አፈጉባኤ እንዲሁም ወይዘሮ ቱሩንጎ ምክት አፈጉባኤ በመሆን በማድረግ በሙሉ ድምፅ ማፅደቁ ይታወቃል።

በጉባኤው የተለያዩ የመንግስት ተጠሪ መሠየም እንዲሁም የዞኑ አስፈጻሚ አካላት ሹመት በምክር ቤቱ አቅርበው ያጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

1 thought on “አቶ አክሊሉ ለማ የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳደሪ በመሆን ተሾሙ”

Comments are closed.