እውቅናውን የሰጣቸው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ሲሆን የሰጠበትም ምክንያት መምህራን የመኖሪያ ቤት እንዲያገኙ በማድረጋቸውና ስልጣናቸውን በሰላማዊ መንገድ በማስረከባቸው እንደሆነ አስታውቋል።
ማህበሩ ከሳቸውም በተጨማሪ ለመምህርና ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደ እውቅና በመስጠት የማህበሩ አንባሳደር እንዲሆኑ መርጧቸዋል።
የኢቢኤስ ጋዜጠኛ የሆኑት ዮናስ ከበደ መምህርነትን በመልካምነት ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፣ በሙያውም አገልግለዋል ለዚህም እውቅና ያስፈልጋቸዋል ያለው ማህበሩ የዋንጫ ሽልማት እንዳበረከተላቸውም ተሰምቷል።
ማህበሩ 22ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአርባ ምንጭ ከተማ እያካሄደ መሆኑን ከኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
