በቅርቡ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ የምክክር መድረክ ላይ የሚሳተፉ አካላት የሚወሰነው በተሳታፊዎች በራሳቸው እንደሚሆን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ብሔራዊ የምክክር መድረኩን በበላይነት የሚያስተባብረው የሰላም ሚኒስቴር ለሪፖርተር በላከው ማብራሪያ ግን በኅዳር ወር የሚካሄደው ዋናው ብሔራዊ የምክክር መድረክ ሳይሆን ስለመድረኩ ሕዝባዊ ግንዛቤ መፍጠሪያና ማሳወቂያ ውይይት እንደሆነ አስታውቋል፡፡

በዚህ የማስተዋወቂያ ፕሮግራም ላይ የሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎችንና ተቋማትን ለሚወክሉ ጥሪ እየተደረገ መሆኑንና እስካሁን ጥሪ ያልደረሳቸው ካሉም በድጋሚ የሚታይ እንደሆነ የሰላም ሚኒስቴር አመልክቷል፡፡

እንደ ሪፓርተር ዘገባ ዋናው ብሔራዊ የምክክር መድረክ መቼ እንደሚካሄድ የሰላም ሚኒስቴር ባይገልጽም፣ በመድረኩ ላይ የሚሳተፉ አካላት የሚወሰነው ግን በራሳቸው በተሳታፊዎቹ እንደሆነ አስታውቋል፡፡