የአርሶአደሩን ሁለንተናዊ ልማት ለማረጋገጥ የሚያግዙ የምርት ግባዓቶችን ዘመናዊ አሰራር ተከትሎ እያቀረበ መሆኑን ዳሞታ የዎላይታ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒዮን ገለፀ፡፡
ዩኒዬኑ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ከ5 በላይ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የግብርና ምርት ግብዓቶች ማቀነባበሪያ ማዕከል ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩም ተነግሯል፡፡
ዳሞታ የዎላይታ ገበሬዎች ህብረት ስራ ኃላፍነቱ የተወሰነ ዩኒዮን በ1966 ዓ.ም በ26 መሰረታዊ ማህበራትና 205 ሺህ ብር ካፒታል የተመሰረተ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በማሳደግ በአሁኑ ወቅት ወደ 70 መሰረታዊ ማህበራትና ወደ 29 ሚሊዮን የሚጠጋ ካፒታል መድረሱን ከዩኒዬኑ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።
ወ/ሮ አለምቱ ጫምሶ በዩኒዬኑ የስራ ዕድል ያገኙ ሲሆን ለተቋሙ ሁለንተናዊ ለዉጥና ዕድገት ከሌሎች የስራ ባልደርቦቻቸዉ ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ተናግረል፡፡ በተላይም አርሶአደሮችና መሰረታዊ ማህበራት ከተለያዩ ወረዳዎች በሚመጡበት ወቅት ቀልጣፋና ተገቢ አገልግሎት እንደሚሰጡም ወ/ሮ አለምቱ አክሏል፡፡
በየወቅቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን እያሻሻለ በዘመናዊ አሰራር ታግዞ በአርሶአደሩ ፍላጎት ላይ ተመስርቶ የምርት ግብዓቶችን በማቅረብና በስሩ ከሚገኙ መሰረታዊ ማህበራት በመግዛት የበኩሉን ሚና እየተጫወተ መሆኑን የዩኒዬኑ ቦርድ ፀሃፊ የሆኑት አቶ ድምሴ ዳና አብራርቷል፡፡ የአርሶአደሩን ሁለንተናዊ ልማት እንቅስቃሴ መደገፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ዩኒዬኑ እየሰራ እንደሚገኝም አቶ ደምሴ ተናግረዋል፡፡
ዳሞታ የዎላይታ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒዮን ስራ አስክያጅ አቶ መስቀሌ በቀለ ዩኒዬኑ ሲመሰረት በ26 ማህበራትና በ205 ሸህ ብር የተመሰረተ ቢሆንም ተቋሙን በተጠናከረ ከባሙያዎች ቅንጅትና አሰራር ለዉጥ ዘዴ በመመራቱ በአሁኑ ወቅት 70 መሰረታዊ ማህበራትና ወደ 29 ሚሊዮን የሚጠጋ ካፒታል ማድረስ መቻሉን አብራርተዋል።
ዩኒዬኑ ጊዜዉንና ወቅቱን ባገናዘበ ሁኔታ በአርሶአደሮችና ተገላጋዮች ፍላጎት ላይ መሰረት አድርጎ በወስጡ ያቀፋቸዉን መሰረታዊ ማህበራትን በተገቢዉ በመምራት እንዲሁም ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በአከባቢዉ ዕድገት ላይ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑንም አቶ መስቀሌ ተናግረዋል፡፡
በተላይም አርሶአደሮች በዘመናዊ ግብርና ምርት ግብዓት እጥረት እናዳይጋለጡና ያመረቱትን ምርት ገበያ አጥቶ እንዳይቸገሩ ዩኒዬኑ በማህበራቱ በኩል ግዢ በመፈፀም መልሶ ለምርት ፈላጊዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እያከፋፈሉ እንደሆነም አቶ መስቀሌ ገልጸዋል፡፡
ዩኒዬኑ በዋናነት ለአርሶአደሮች የግብርና ምርት ግብዓቶችን በተለይም የአፈር ማዳበሪያ፣ ስኳር፣ የተላያዩ ምርጥ ዘሮችንና በራሱ ማቀነባበሪያ ፋብርካ የሚያመርተወን መኖ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በስሩ በሚገኙ ማህበራት በኩል እያከፋፈለ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል ዩኒዬኑ የተላያዩ ምርቶችን ከአርሶአደሮች ገዝቶ በራሱ መጋዘን በማከማቸት መልሶ ለአርሶአደሮች በመሸጥ እንዲሁም ወደ ዉጭ ሀገር እንደምልክ ጠቁመው ለአብነትም ዘንድሮ ቡናን በራሱ ማፈልፈያ ጣቢያ በማዘጋጀት ከ750 ሺህ በላይ ዶላር ማግኘቱንም ኃላፊው አብራርተዋል፡፡
ወቅቱ የሚጠይቀዉን ግብዓት ለአርሶአደሩ እያቀረበና ከአምራች አርሶአደሮች ምርታቸውን እየገዛ ተቋማዊ አደረጃጀትንና አቅምን በማሳደጉ በደቡብ ክልል ሁለተኛ የሆነው ዩኒዬኑ የአርሶአደሩን የመልማት ፍላጎት በዘመናዊ አሰራር መተካት የሚያስችል ግዙፍ የግብርና ግብዓቶች ማቀናባበሪያ ማዕከል ለመገንባት በዎላይታ ሶዶ ከተማ 5.2 ሄክታር መሬት በመረከብ ወደ ስራ ለመግባት የሚስችል እንቅስቃሴ እያደረገ ቢሆንም ስራዉን በሚፈለገዉ ልክ ለማከናወን ከፍ ያለ ገንዘብ የሚያስፈልግ በመሆኑ የብድር አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትና የሚመለከታቸዉ አካላት ለስራዉ ስኬታማነት እንዲተባበሩም ሥራ አስክያጁ ጥሪ አቅርቧል ሲል የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል፡፡


