የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በዛሬው ዕለት ለመምህራን የማህረግ ዕድገት (Promotion) ሰጠ። (ጥቅምት 16/2013ዓ.ም-ወሶዩ)

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለ 32 መምህራን የተባባሪ እና የረዳት ፕሮፌሰርነት ማህረግ ዕድገት (Promotion) መስጠቱ ተገለጸ።

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በዛሬው ዕለት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ተወያይቶ ካጸደቃቸው ውሳኔዎች መካከል የመምህራን የተባባሪነት እና የረዳት ፕሮፌሰርነት የማህረግ እድገት ውሳኔ 1ኛው ነው።

የዩኒቨርሲቲው ህገ-ደንብ/ሌጅስሌሽን በሚፈቅደው መሰረት የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ከተሰጣቸው 32 መምህራን መካላከል ሃያ ዘጠኙ(29) በረዳት ፕሮፌሰርነት የተቀሩት ሶስት(03) ደግሞ በተባባሪ ፕሮፌሰርነት የማህረግ እድገት (Promotion) ማግኘታቸው ተገልጿል።

የደረጃ ዕድገቱ በዩኒቨርሲቲው ከሚተዳደሩ 3ቱም ካምፓሶችና ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ለተወጣጡ መምህራን የተሰጠ እንደሆነም ሴናተሮቹ ባዳረጉት ውይይት ተጠቁሟል።

ለማህረግ እድገት የተወዳደሩ መምህራን በመማር ማስተማር፣ በችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግርና ስርጸት መስክ ያስመዘገቡት ውጤት በየደረጃው በሚገኙ የስራ እርከኖች ከማህደራቸው ተፈትሾ እንዲሁም ለዕድገቱ የተቀመጡ መመሪያዎችንና መስፈርቶችን ማሟላታቸው ተረጋግጦ የተሰጠ መሆኑም ተገልጿል ።

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በዛሬው እለት የቀረበለትን የማህረግ እድገት ጥያቄ በሚገባ መርምሮ ለ 32 መምህራን የተባባሪነት እና የረዳት ፕሮፌሰርነት ማህረግ ያጸደቀ ሲሆን፤ ለዩኒቨርሲቲው መምህራን የሚሰጠው የማህረግ እድገት በቀጣይ ጊዜያትም የተቋሙ ህገ-ደንብ (ሌጅስሌሽን) በሚፈቅደው አግባብ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።

በዛሬው እለት በተባባሪነት እና በረዳት ፕሮፌሰርነት ደረጃ የማህረግ እድገት ያገኛችሁ ውድ የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር መልካም ምኞቱን ይገልጻል ሲል የዩንቨርሲቲው ኮሙኒኬሽን ዳይሮከተሬት ዘዘግቧል !!🙏🙏