
የበጋ መስኖ ልማት ያለፋትን ተሞክሮዎች በመቀመር በበጋ መስኖ የስንዴ ልማት በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ 

በዎላይታ ዞን የበጋ መስኖ፤ የአረንጓዴ አሻራና የቡና ምርት ጥራት ቁጥጥርና ግብይት ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
የበጋ መስኖ ልማት ያለፋትን ተሞክሮዎች በመቀመር በበጋ መስኖ የስንዴ ልማት በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ እንደገለጹት ዘንድሮ በመስኖ የማይለማ አርሶአደር እንዳይኖር ግብ ተጥሎ በልዩ ሁኔታ ይሰራል ብለዋል።
በዞኑ ባሉ የመስኖ አውታሮችን አሟጥጠን በመጠቀምና አብዛኛውን አርሶአደርን ተደራሽና በልማቱ ተሳታፊ በማድረግ የመስኖ ልማት ምርት ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራም ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።
በ2014 ዓ.ም የበጋ መስኖ ልማት ያለፋትን ተሞክሮዎች በመቀመር በበጋ መስኖ የስንዴ ልማት በትኩረት እንደሚሰራ የዎላይታ ዞን ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አድማሱ አወቀ አስታውቀዋል።