በ
የዉጭ ምንዛሪያችንን የሚያስድግ ቀዳሚ ቡና እንደሆነ ዋና አስተዳደሪው ጠቅሰው አመራች አርሶአደሮቻችን በቡና ዙሪያ ተገቢውን ግንዛቤ ወስደው የቡና ጥራቱን በአግባቡ ከያዙ በሀገር ደረጃ ተወዳዳሪ ሊሆን እንደሚችሉ አሳስበዋል፡፡
ማሳዎቻችን በዘላቂነት ምርትና ምርታማነቱን ጠብቀው እንዲቀጥሉ ማድረግ፣ የአከባቢያችን አየር ንብረት እንዳይዛባ ምዛኑን ጠብቀው እንድኖር የተተከሉ ችግኞች ውጤታማ እንዲሆኑ ልዩ እንክብካቤ ማደረግ እንዳለበት ዋና አስተዳዳሪው አሳስበዋል፡፡

በግብርና ዘርፉ የሚሰራው ሥራ ለነገ የማይባልና የሀገራችን ትኩረት አቅጫጫም ጭምር እንደሆነ የዎላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነ አስታውቀዋል፡፡
የዘንድሮ የበጋ መስኖን ከወትሮ በተለዬ ሁኔታ ይሰራል ያሉት አቶ ዮሐንስ ለዚህም ፓርቲያችን በቀጣይ ጊዚያት የኢትዮጵያ ብልጽግናን እውን አረጋለሁ ብለው ከያዛቸው ቁልፍ አጀንዳዎች አንዱ ነው ያሉት፡፡
ግብርና ሥራን ማዘመንና ህዝባችን ማገልገል ለአማራጭ የሚሰጥ ጉዳይ እንዳልሆነ ሁሉም አካላት አውቀው በቁርጠኝነት መሰራት ያስፈልጋል ብለዋል ኃላፊው፡፡
የዎላይታ ዞን ም/አስተዳደሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አድማሱ አወቀ በበኩላቸው ግብርናችን ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ገበያ ለማረጋጋት፣ የውጭ ምንዛረን ለማሳደግ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ለማስተካከል፣ ምግብ ዋስትናንና ስነ-ምግብ ዋስትናችን ለማረጋገጥ መፍትሔ ብለን በአዲሱ ምዕራፍ አቋም ይዘን እንሰራለን ብለዋል፡፡
የዘንድሮ በጋ መስኖ ልማት ሥራን ለየት የሚያደርገው ከውጭ የሚገባውን ስንዴን ለማስቀረት የበጋ መስኖ ስንዴ በኩታ ገጠምና በተሟላ ተክኖሎጂ ማልማት ወሳኝ ጉዳይ እና ሀገራዊ ተልዕኮ ስለሆን በትግል እንዲመራ አስታዉቀዋል፡፡
ከዞኑ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በዓመቱ 4201.5 ሄክታር መሬት ላይ ስንዴውን በመስኖ በማልማት ከ108 ሺህ በላይ ኩንታል የስንዴ ምርት ለማግኘት በትኩረት እንደሚሰራም ኃላፊው ተናግረዋል።
በንቅናቄው መድረክ የዞንና የወረዳ/ከተማ አስተዳዳር ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ለመድረኩ የተዘጋጁ ሰነዶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርገው የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል።