የ

ባለፈው ሩብ ዓመት ብቻ በዎላይታ ከ480 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉ ተገለፀ
ባለፈው ሩብ ዓመት ብቻ በዎላይታ ከ480 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉ ተገለፀ፡፡

የዎላይታ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ጳውሎስ በዞኑ በተያዘው በጀት ዓመት ከመደበኛ ገቢና ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት 2 ቢሊዮን 4 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ሩብ ዓመት ከመደበኛው ገቢ 404,750, 000 ለማሰባሰብ ታቅዶ 427, 207, 523 ብር መሰብሰብ መቻሉንና አፈጻጸሙም በመቶኛ 105.7% መሆኑንና እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ብር 96, 250,000 ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 59,041,471.69 አቶ መብራቱ አብራርተዋል፡፡

በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከመደበኛና ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ብር 501, 000,000 ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 486, 608, 995 መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን አፈጻጸሙም 97.8 በመቶ መሆኑንና ይህ አፈጻጸም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ሲነጻጸር በብልጫ ብር 217 368 194 መሆኑ ታውቋል፡፡

ደረሰኝ መስጠት ከግብር ህግ ግዴታዎች አንዱና ዋናው ሆኖ ሳለ ይህንን ግዴታ ባልተወጡ 38 ግብር ከፋዮች በእያንዳንዱ ላይ 50 ሺህ ብር መቀጫ መጣሉ ተገለጿል፡፡

የደረጃ “ሀ” ግብር ከፋይ ግብር የሚከፈልበት ጊዜ ከሐምሌ 2013 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 30/2014 ዓ/ም በመሆኑ ሁሉም የደረጃው ግብር ከፋይ የሚጠበቅበትን ግብር ከቀኑ አስቀድሞ በመክፈል ሊደርስ ከሚችለው መጨናነቅ ራሱን እንዲያድን ባለስልጣን ጽ/ቤቱ አሳስቧል፡፡

በዎላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪ ከሆኑት ግብር ከፋዮች አንዳንዶቹ እንዳሉት ግብር መክፈል የዜግነት ግዴታ በመሆኑ የሚጠበቅብንን ግዴታ ማንም ሳያስገድደን እየተወጣን እንገኛለን ብለዋል፡፡

ደረሰኝ በመጠየቅ ሁላችንም የዜግነት ድርሻችንን እንወጣ!