በናትናኤል ጌቾ-

የፌስቡክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ የድርጅታቸው አዲሱ ስያሜ ” ሜታ (Meta)” መሆኑን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
አዲሱ ስያሜ ኩባንያው በቅርቡ ለመጀመር ካሰበው “ሜታቨርስ” ከሚለው የተወሰደ መሆኑንም ገልፀዋል።
ፌስቡክ የኩባንያውን መጠሪያ “ሜታ” በሚል ቢቀየርም በኩብንያው ስር የሚገኙት የማህበራዊ ትስስር ገጾች ማለትም ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ፣ ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር የቀደመ ስማቸውን ይዘው እንደሚቀጥሉ ኩባንያው አስታውቋል።