
የዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ታፍነው የሚወለዱ ህፃናት በተገቢው እንዲተነፊሱ ለመርዳት የሚያስችል የክህሎት ሥልጠና ከ17-19/02/2014 ዓ.ም ድረስ ለ03 ተከታታይ ቀናት የተለያየ ሙያ ስብጥር ላላቸዉ የጤና ባለሙያዎች በተለይም ከእናቶችና ሕፃናት ጤና አገልግሎት ዘርፍ (MCH) ለሚሰሩ ዎላይታ ዞን ከሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች ለመጡ የጤና ባለሙያዎች መሆኑን ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ቺፍ ምርምርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳሬክተር መ/ርት ባንቺዓለም ነጋ ረዳት ፕ/ ር ተናግረዋል፡፡
የሥልጠናዉ ዓላማ ጨቅላ ሕጻናት እንደተወለዱ የመጀመሪያ ትንፋሽ እንዲያገኙና ታፊነዉ የሚወለዱ ህጻናት በተገቢዉ እንዲተነፍሱ ለመርዳት የሚያስችል ክህሎት የሚያስጨብጥ ሥልጠና መሆኑን መ/ርት ባንቺዓለም ነጋ ገልጻለች፡፡
ስልጤናዉን የዩኒቨርሲቲዉ ምርምርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ምክትል ፕረዚዳንት ጽ/ቤት እና ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ቺፍ ምርምርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳሬክተር ጽ/ቤት በጋራ አካሂዷል፡፡
ዶ/ር ዳዊት ዳልጋ የዎ.ሶ.ዩ ምርምርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እና ተሳትፎ ዳይሬክተር በበኩላቸው፣ የዩኒቨርሲቲው ካአሉን 7(ሳባት) ኮሌጆች እና 3(ሶስት) ት/ት ቤቶች ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ በሚሰጠው ዘርፈ ብዙ የጤና አገልግሎት ለማህበረሰባችን ቅርብ የሆነ ኮሌጅ መሆኑ እውን ነዉ ብለዉ፤ ከጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ የጤናዉን ዘርፍ ክፍተቶችን ለመሙላት የሚሠሩ ፕሮጀክቶች እንዲጠናከሩና አዉንታዊ ምላሽ እንደሚያገኙም ተናግሯል።
የጤናዉን ሴክተር የሚደግፍ በዋናነት ጨቅላ ሕጻናትን አተነፋፈስ ችግር ጋር ተያዩዞ ያለዉን ችግር እንዲረዱ የባለሙያዎች አቅም ለማጎልበት የኮለጁ መምህራንና ተማሪዎች እያበረከቱ ላሌዉ ሚና አመስግነዉ፤ ሠልጣኞች ለባልደረቦቻቸዉ ዕዉቀትን በማጋራት የድርሻቸዉን እንዲወጡ ዶ/ር ዳዊት አሳስበዋል።
መ/ርት ባንቺዓለም ነጋ ሥልጠናዉ ለሁለተኛ ዙር የተሰጠ በመሆኑ በቀጣይ ተፈፃሚነቱን ሥራ ቦታቸዉ ድረስ በመዝለቅ ክትትልና ድጋፍ ተጠንክረዉ እንደሚቀጥል ገልፀዋል ፡፡