የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዎላይታ ዲስትሪክ ላበረከተው የልማት አስተዋጽኦ የአካባቢው ህብረተሰብ ምስጋና አቀረበ።
መስሪያ ቤቱ ቢሮ ዋና መቀመጫ ባለበት አከባቢ ከ3 ሚልዮን ብር በላይ በሚገመት ወጪ የመሠረተ ልማት ሥራዎችን ሠርቶ ለአውራጎዳና መንደር ህብረተሰብ አስረከበ።
አዲስ የጥርጊያ መንገድ መክፈት፣ ጠጠር መንገድ ማልማት፣ የዲች ኪዳን መዘርጋት እና ሌሎች ሥራዎች ተቋሙ ከሠራቸው ሥራዎች የሚጠቀሱ ናቸው።
በዚህም የአካባቢው ህብረተሰብ ለዘመናት ሲቸገሩበት የቆዩት ችግር ስለተቀረፈላቸው ለተቋሙ ልባዊ ምስጋና እና ዕውቅና ሰጥተዋል።
የዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደርም ለመስሪያ ቤቱ የምስጋና እና ዕውቅና ምስክር ወረቀት ሰጥቷል።
ተቋሙ በዚህም ብቻ ሳያበቃ ቀጣይ በአካባቢው የመንገድ ዳር መብራት ለመዘርጋት፣ አረንጓዴ ቦታዎችን ለማልማት እና ሌሎች የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ ቃል ገብቶላቸዋል።


