በዎላይታ ባለፈው ክረምት ወራት ወጣቶች በጎ ፊቃድ አገልግሎት በ12 አገልግሎት ዘርፎች 254 ሺህ ወጣቶችን በማሳተፍ ከ222 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ከመንግስት ወጪ ለማዳን ተችሏል

በዎላይታ ዞን በ2013 ዓ.ም የተካሄደ የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፊቃድ አግልግሎት ማጠቃለያ እና የ2014 ዓ.ም በጋ ወራት መክፈቻ ዞናዊ መድረክ ተካሂዷል፡፡

ማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አክሊሉ ለማ እንዳሉት የበጎ ፊቃድ አግልግሎት ስራ ከህዝብ ለህዘብ በህዝብ መሆን እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡

በጎ ስራ መልካም መንፈስን ያስረጻል፣ ተስፋ የሚያደርግ ህብረተሰብን ክፍልን ይፈጥራል፣ ብሩህ ተስፋን ያሰፋል እንድሁም ቅም በቀልና ጥላቻን ከሰዎች ዘንድ እንዲጠፋና መልካምነት እንዲሰፊን ያደርጋል ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው፡፡

ህብረተሰቡ በየአከባቢው ተደረጃተው አከባቢውን መጠበቅ እንዳለባቸው ዋና አስተዳዳሪው ጠቅሰው በዞናችን በሁሉም አከባቢዎች የሰላምና ፀጥታ ስጋት እንዳይኖርና ህዝቡ በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገባ ወጣቱ የበኩሉን ሚና መወጣት እንዳለበት ጠይቀዋል፡፡

የበጋ መስኖና በጎ ፊቃድ አገልግሎት፣ የቡና ምርት ጥራት ቁጥጥርና ግብይት እና ዕድሜው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲገቡ ሁሉም ህብረተስብ ክፍሎች የበኩላቸው ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በበጎ ተግባር ለመሳተፍ እድሜ የማይገድብ እንደሆነና እየተስፋፋ የመጣውን የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነ አሳስበዋል፡፡

ሥራ አጥነትን በመንግስት ሥራ ብቻ መቀነስ አያቻልም ያሉት አቶ ዮሐንስ ወጣቶች በተለያዩ ሥራ ክህሎት ተጠቅመው የስራ አመራጮችን መፈለጊ እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡ 

ወጣቶች በዞኑ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ላይ ጉልህ ተሳታፊና በተሳተፏቸው ልክ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተለያዩ ጥረቶች መደረጉን የዎላይታ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታደሴ ተክሌ ገልጸዋል፡፡ 

የዎላይታ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትል እና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ ወጣት ሚካኤል ዋዳ በበኩሉ በዞኑ የ2013 ክረምት ወራት ወጣቶች በጎ ፊቃድ አገልግሎት በ12 አገልግሎት ዘርፎች 254 ሺህ ወጣቶችን በማሳተፍ ከ222 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ከመንግስት ወጪ ለማዳን የተቻለ ሲሆን ከ889 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በሁሉም ተግባር የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ መዋቅሮችና ለዘርፉ ወጤታማነት አስተዋዖኦ ላደረጉት አካላት የሰርትፌከትና የዋንጫ ሽልማት ተበረክቶላቸዋል፡፡