በሽብርተኛው ህወሃት ቡድን የሰሜን እዝ ከጀርባው የተወጋበትን 1ኛ ዓመት በማስመልከት የሻማ ማብራት ስነ ስርዓትና በአሸባረው በሽብር ቡድኑ ለተሰው ጀግኖች የ1 ደቂቃ የህሊና ጸሎት ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

አቶ ተወልደ ተስፋዬ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ሲሆኑ መከላከያ ሰራዊት ለኢትዮጵያ ዘላለማዊ ክብር የከፈለውን ዉድ የመስዋዕትነት ጥግ ምንጊዜም በታሪክ እየዘከርን የሚንቆይ ነው ብለዋል።

ጥቅምት 24 ቀን ከሃዲውና አሸባሪው የህውሃት ጁንታ ቡድን በአገራችን በሰሜኑ ዕዝ መከላከያ ሰራዊታችን ክህደት የፈጸመበትና ዘግናኝ ጭፈጨፋ ያካሄደበት አንደኛ አመትን በማስመልከት ነው መልዕክት ያስተላለፉት።

ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም ፤ ሀገራችንን ሳናስደፍር አካባቢያችንን በመጠበቅና መከላከያ ሠራዊታችንን በመደገፍ ልሆን ይገባል ሲሉ በአጽንኦት ተናግረዋል።

የዲላ ከተማ ከንቲባ አቶ ተስፋጽዮን ዳካ በመከላከያ ሰራዊታችን የተፈፀመው ጥቃት አፀያፊ ከመሆኑም ባሻገር ሀገርቷን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ ለሚሯሯጥ ለሽብር ቡድን እድል ሳንሰጥ አካባቢያችንን በመጠበቅ ልሆን ይገባል ሲሉ ተደምጧል።

በዕለቱ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ ተከናውኗል።

በመድረኩም የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት መምሪያ ሀላፊ ዕጩ ዶ/ር ዝናቡ ወልደ ፣የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተወልደ ተስፋዬ፣ ከፍተኛ የዞን የዲላ ከተማና ቀበሌ አመራሮች፣ በዞኑ የሚገኙ መመሪያ ማናጅመንት አካላት ተገኝተዋል።