ባለፈው ታህሳስ ወር በድንገተኛ እሳት አደጋ የተቃጠለውን የመርካቶ ገበያ በዘመናዊ መንገድ መልሶ ለመገንባት የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ቅኝት ባደረገበት ወቅት አረጋግጧል።
አጠቃላይ የግንባታ ስራው ባለቤት በዘርፉ ልምድ ያለው ኢዳብ የተሰኘ የአለምአቀፉ ኩባኒያ ሲሆን ግንቦታውን እያከናወኑ የሚገኙ ተቋራጮች መካከል የአንጆንዮ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭ እህት ኩባንያ የሆነው የታደሰ ሮባ ጃርሳ ጠቅላላ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ እና የታደሰ ወንድወሰን ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የገበያ ማዕከል ግንባታው በተቀመጠው ጊዜ ገደብ እና በጥራት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፅዋል።
የገበያ ማዕከሉ ብዙ ዜጎች ሰርተው የሚለወጡበትና ከዕለት ተዕለት ህይወታቸው ጋር የተቆራኘ ቦታ በመሆኑ በድርብ ኃላፊነት በጥራትና በጊዜ ለመጨረስ ሙሉ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆኑን የአንጆንዮ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭ እህት ኩባንያ የሆነው የታደሰ ሮባ ጃርሳ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እና የታደሰ ወንድወሰን ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ባለቤቶች ተናግረዋል።
በተለይም በአሁኑ ወቅት የገበያ ማዕከሉ ግንባታ ዋና ዋና የሚባሉ ስራዎች በመጠናቀቁ ወደ መጨረሻ ምዕራፍ ለመግባት የሚያስችል ዘመናዊ የኢሳት አደጋ ተጋላጭነት የሚከላከሉ ግድግዳ መግጠምና ተያያዥ ስራዎች ተጠናቅቆ በቅርቡ ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተቋራጮቹ አስረድተዋል።
የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የግንባታ ሂደቱን ቅኝት ባደረገበት ወቅት ስራው በተቀመጠው ጊዜ ገደብና ጥራት ለማጠናቀቅ እርብርብ እያደረጉ እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላትና ባለሙያዎች ክትትል እያደረጉ ሲሆን በርካታ የገበያ ማዕከሉን መጠናቀቅ በተስፋ የሚጠብቁ ዜጎች በዙሪያው በመንገድ ዳር በማይመች ሁኔታ ውስጥ ሆነው የንግድ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ለመመልከት ችለናል።
የመርካቶ ገበያ መልሶ ግንባታ በየ100 ሜትር የእሳት አደጋ ለመከላከል የሚያስችል የውሃ ቋት፣ የአስፋልት መንገዶች፣ የውሃ እና የዲች መስመር፣ የተሽከርካሪዎች ማቆሚያ እና የቁም እንስሳት ጊዜያዊ ማቆያ የማዕከሉ የግብይት ሂደቱን የሚያዘምን የአዲሱ የዎላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ ገበያ ማዕከል አካል ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 24/02/14 E.C , Sodo, Ethiopia
