ሀገሪቷ ከገጠማት ችግር በድል እንድትወጣ በተባበረ ክንድ ለመመከት መዘጋታቸውን የዎላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ።

በከተማዋ ለሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ከመስጠት ባለፈ አካባቢውን ከወትሮው በተለየ መንገድ ለመጠበቅ የሚያስችል ህብረተሰብን የሚያሳትፍ አሰራር ዘርግቶ እየሰራ መሆኑን የሶዶ ከተማ ፓሊስ ፅ/ቤት አረጋግጧል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዛሬው ዕለት በከተማዋ ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ባደረገው ቆይታ በአሁኑ ወቅት አሸባሪው ህወሃት የሀገሪቱን ህልውና ለመፈታተን እያደረገ የሚገኘውን እኩይ ተግባር በፅኑ አውግዟል።

በልጆቿ መስዋዕትነት ነፃነቷን አስጠብቃ የቆየች ሀገር ዛሬም በውስጥ ባንዳዎችና በአሸባሪዎች ሴራ አትፈርስም ሲሉ በከተማዋ ዞሬን ያነጋገርናቸው መምህር ማሞ አይካ እና አቶ ደስታዬ ሚጣ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን በብሔር፣ በኃይማኖትና በጎሳ በማከፋፈል ስመዘበር የነበረውና በህዝብ የተባበረ ክንድ ከስልጣን የተወገደው ይኸው ኃይል ሀገር የማፍረስ በያዘው ተልዕኮ በአማራና አፋር ክልሎች በንጹሀን ላይ እያደረሰ የሚገኘውን ግድያና ማፈናቀል እንደሚያወግዙም መምህር ማሞ እና አቶ ደስታ አስረድተዋል።

ሌላኛው አስተያየት ሰጪ የሆኑት ወጣት ቢኒያም ማጉሌ እና ወይዘሮ ድንቅነሽ መና ይሄንን አጥፊ ቡድን በተባበረ ክንድ ለመደምሰስ በሚደርገው ትግል ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን በመቆም በገንዘብ፣ በዓይነትና በሞራል እንዲሁም ተደራጅቶ አከባቢያቸውን በመጠበቅ የጀመሩትን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥሉም የከተማ ነዋሪዎቹ አስተያየታቸውን ሰጥቷል።

የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከሰባት በላይ መግቢያ መውጫ ያለባት ለበርካታ ስዎች መተላለፊያ ከተማ በመሆኑ ከተማዋ ላይ ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ከመቸውም ጊዜ በላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የሶዶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ተወካይ ሻለቃ መሉ ሙንኤ ተናግረዋል።

በተላይም በአሁኑ ወቅት ሀገራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መንገድ ህብረተሰቡ በየአካባቢው ተደራጅተው አከባቢውን ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ለመጠበቅ የሚያስችል አሰራር ተዘርግቶ እንቅስቃሴ መጀመሩን ሻለቃ ሙሉ አስረድተዋል።

ህብረተሰቡ ማናቸውም የፀጥታ ስጋት አዝማሚያ ሲያጋጣም ለአከባቢው ፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት የዜግነት ኃላፊነት እንዲወጣ ሻለቃ መሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።

Wolaita Times, 25/02/14 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹