ኢትዮጵያውያን ብሔራቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘው እንዲንቀሳቀሱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያስገድዳል ሲል ሬውተርስ ያወጣው ዘገባ ሐሰተኛ መሆኑን የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዜጎች የመሥሪያ ቤት መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ እና ፓስፖርት ይዘው እንዲገኙ እንደሚጠይቅ የገለጸው ማጣሪያው፣ በእነዚህ ሁሉም ላይ ብሔርን ለመግለጽ የሚያስገድድ ሁኔታ እንደሌለ ገልጿል።
በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ በርካታ የከተማ አስተዳደሮች መታወቂያ ላይ ብሔርን የመግለጽ ግዴታን እያስቀሩ እንደሆነ ነው ማጣሪያው ያስታወቀው።
ሬውተርስ ይህን ሐቅ ግምት ውስጥ ሳያስገባ በዚህ መልኩ መዘገቡ የዜናው ጻፊ እና አርታኢ ኃላፊነታቸውን ወደ ጎን ስለመተዋቸው ግልጽ ማሳያ ነው ብሏል የወቅታዊ ሁኔታ ማጣሪያ።
