የዎላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ቅድመ ወንጀል መከላከልና ጥናት ማስተባበሪያ ኃላፊ ዋና ኢ/ር በጋሻው ባልቻ በዞኑ ባሉት በሁሉም የፍተሻ ኬላዎች የተጠናከረ የፍተሻ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው በዞኑ ባሉት የፍተሻ ኬላዎች ላይ የህግ አካላት አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ የአከባቢውን ሰላም ማስጠበቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ኃላፊው አክለውም ህብረተሰቡ አካባቢያቸውን በንቃት በመጠበቅና የተለየ እንቅስቃሴ በሚያዩበት ጊዜ ለህግ አካላት  መጠቆም እንዳለባቸውና የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በዎላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኮ/ር  ያሊሳ ጋጋ በበኩላቸው በወረዳችን ባለው በቡጌ  ኬላ ላይ ከወትረው በተለየ መልኩ የሰዉ ሀይልና ጥንቃቄ በተሞላ መልኩ ነቅተን እየጠበቅን ነው ብለዋል።

አዛዡ አያይዘውም ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጎን መሆናቸውን ተናግረዋል።

በፍተሻ ስፍራ የዞዞኑ መኮጉመ ያነጋገረው አሽከርካሪ ወጣት ፈቃዱ አሰፋ እንደዚህ መፈተሽ እጅግ በጣም አስፈላጊና ተገቢ መሆኑን ገልጾ የህግ አካላት ከመቸውም ጊዜ በላይ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ብሏል።

አሽከርካሪው አክሎም እኛ አሽከርካሪዎች ዝም ብለን ተሳፋሪ  ስላገኘን ብለን መጫን የለብን፤ ማን ወዴት እንደሚሄድ ጠይቀን አጣርተን እኛም ለዚህች አገር የድርሻችንን ማበርከት አለብን ሲል አሳስበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *