የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በስፔን ሀገር የሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችን በመጎብኘት የልምድ ልውውጥ እያደረጉ ይገኛሉ።

በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዬች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ዴአ፣ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብርሃም ቦሻ፣ የቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተክሌ ሌዛ፣ የሕግ ትምህርት ቤት ዲን  መምህርት ሃዊ አስፋው እንዲሁም የኢንፎርማቲክስ ትምህርት ቤት ዲን መምህርት ፈጠነች መስቀሌ በሀገረ ስፔን በሚገኙ አራት አንጋፋ ዩኒቨርሲቲዎች ጉብኝት እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል።

በሀገሪቱ አንጋፋ ከሆኑ አራት ዩኒቨርሲቲዎች   የባርሴሎናው አውቶኖሚ ዩኒቨርሲቲ፣ ፑምፔ ፋበር ዩኒቨርሲቲ፣ የማድሪድ አውቶኖማ ዩኒቨርሲቲ እና የካርሎ ዩኒቨርሲቲ-3 የጉብኝቱ አካል እንደሆኑ ተጠቁሟል።

ከአራቱ የስፔን ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በተደረገ የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት በሰላም መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን፤ አለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር፥ የጋራ ሥርዓተ ትምህርትን ማልማት፥ ለፒኤችዲ እና ማስተርስ የትምህርት መርሃግብሮች ስኮላርሺፕ ማመቻቸት፥ የሰራተኞች እና ተማሪዎች ልውውጥን ማጠናከር፥ የጋራ ምርምር እና ፕሮጀክቶችን ማስፋፋት እንዲሁም በግብርና፣ በጤና፣ በቴክኖሎጂ እና በቱሪዝም እና መስተንግዶ አስተዳደር ላይ ምርጥ ተሞክሮዎችን ማሰስ የስምምነቱ አበይት ዓላማዎች መሆናቸውን የዩንቨርስቲው ኮጉዳ ጠቁሟል።

ከአራቱ ዩኒቨርሲቲዎች የተገኙ ልምዶችን በመቀመር ዘላቂ ለውጥ ማምጣት በሚያስችል መልኩ መስራት ተገቢ እንደሆነ ጎብኚዎቹ አሳውቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *