በዎላይታ ሶዶ ከተማ እንያት ሆስፒታል ከሁለት ሳምንታት በሁዋላ ሙሉ ዝግጁቱን አጠናቆ በተደራጀ መንገድ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችለው ሰሞኑን በሆስፒታሉ የተለያዩ ባለሙያዎችን አወዳድሮ ለመቅጠር የስራ ማስታውቂያ ባወጠው መሠረት እያወዳደረ መሆኑን የሆስፒታሉ አስተዳደር ማሳወቁን መዘገባችን ይታወሳል!
ነገር ግን ሆስፒታሉ ከአመልካቾች በተደጋጋሚ በቀረበው ጥያቄ መሠረት በነገው ዕለት ዕሁድ 05/03/14 ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ በተጨማሪነት አመልካቾችን የምቀበል መሆኑን በመግለፅ በትርፍ ሰዓት እና በእረፍት ቀናት ከድርጅቱ ጋር ለመስራት ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች የምስተናግዱት ከ7-8/03/14 ዓ.ም ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ ዝግጅት እንድታደርጉ በሚል የሆስፒታሉ አስተዳደር አስተውቋል።
በዎላይታ ሶዶ ላለፉት አስራ ሶስት ዓመታት ዘመናዊ ህክምናን በማስተዋወቅና በመስጠት የሚታወቀው እንያት ክሊኒክ ማስፋፊያ አካል የሆነው ይህ እንያት ሆስፒታል እጅግ በተራቀቁ ዘመናዊ መሳርያዎችንና ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች አደራጅቶ ወደ ስራ በሚገባበት ጊዜ በከተማው በዞኑ እንዲሁም አጎራባች አከባቢዮች ላይ ተመራጭና አማራጭ የህክምና ማዕከል በመሆን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሊኖሩ የሚችሉ የታካሚ ሪፈራልን ሙሉ ለሙሉ ለማስቀረት የሚያስችል የህክምና ተቋም እንዲሆን በራሱ ባስገነባው አዲስ ዘመናዊ ህንፃ የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩም ተነግሯል!!
እንያት ሆስፒታል
አድራሻ ⏩ ዎላይታ ሶዶ ከተማ ከብሩህ ተስፋ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፊትለፊት ያገኛሉ⏬ ስልክ ቁጥር ⏬
0465512916
0913469148
