በዎላይታ ሀገር የማዳን ጥሪ ምላሽ የሰጡ አመራሮችና የቀድሞ ክብር ተሰናባች መከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ግንባር ተሸኙ

ዞኑ ለ5ኛ ጊዜ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ በአይነትና በገንዘብ ለመከላከያ ሰራዊት በዛሬው ቀን መደረጉም ተጠቁሟል።

ከዎላይታ ዞን ከሁሉም ከተማ/ወረዳ አስተዳደር 15 ሚሊዮን የሚሆን የጥሬ ገንዘብና 25 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የተለያየ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገልጸዋል።

ለሀገሪቱ ህልውና የተዋደቁ እንዲሁም እንዲሁም አሁንም ሀገር ለማዳን የሚዘምቱ ጀግና ሰራዊትና በተለያዩ መንገድ አጋሪነታቸው ላሳዩ ወገኖች አቶ አክሊሉ ምስጋና አቅርበዋል።

ከሀብት አሰባሰብ ኮሚቴ የተሰበሰውን ቁሳቁስ ከተተረገበ በኃላ ከዞኑ ከሁሉም ከተማ/ወረዳ አስተዳደር የተወጣጡ አመራሮችና የቀድሞ ክብር ተሰናባች መከላከያ ሰራዊት አባላት ሀገር የማዳን ጥሪውን ተቀብለው በጉታራ አድራሽ ወደ ግንባር ሽኝት ተደርጓል።

“ሀገሬን እጠብቃለሁ መስዋዕትነት እከፍላለሁ” በሚል ከወላይታ ዞን ከሁሉም ከተማ/ወረዳ አስተዳደር የተውጣጡ አመራሮች እና የቀድሞ በክብር ተሰናባች መከላከያ ሰራዊት አባላት የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን ለመቀላቀል እና ድጋፍ የሚሰጡበት  መርሐግብር እየተካሄደ ነው።

በጉታራ አድራሽ እየተካሄደ ባለው የሽኝት ፕሮግራም የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አክሊሉ ለማ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።

Wolaita Times, 04/03/14 E.C , Sodo, Ethiopia