ዩኒቨርሲቲው ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ለመከላከያ ሰራዊት አድርጓል።
ለሁለተኛ ጊዜ ዩኒቨርሲቲው 39 ሚሊዮን ብር በጥሬና 6.5 ሚሊዮን ብር በዓይነት ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ እንደገለፁት መከላከያን መደገፍ ሀገርን መደገፍ በመሆኑ የተጀመረው ሀገር የማዳን ስራ እስኪጠናቀቅ ዩኒቨርሲቲው ደጀንነቱን ይቀጥላል ብለዋል።
የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አገርን ለማዳን እየተዋደቀ ላለው መከላከያ ሠራዊት ለሁለተኛ ጊዜ ድጋፉን ገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው በአይነትና በገንዘብ ያሰባሰበውን ድጋፍ አዲስ አበባ ለሚገኘው ኮሚቴ በነገው ዕለት ሊያስረክብ ዛሬ የዩኒቨርስቲው የድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ወደስፍራው አቅንቷል።
ላለፉት አስራ ሁለት ወራት የአገርን ህልውና ለማስቀጠል ከሚደረገው ትንቅንቅና ትግል ጎን መሆኑን ለማሳየት ዩኒቨርሲቲው በቀደመው ድጋፉ ከብር ሁለት ሚሊየን በተጨማሪ 100 ኩንታል ነጭ ጤፍ አስረክቧል መምህራንንም ማዝመቱን ፕረዚዳንቱ ተናግረዋል።
አገር ስትፈርስ እንደ ዩኒቨርሲቲ መማር ማስተማር፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ መሠረተ ልማት ግንባታ ሊኖር አይችልም፣ ኢትዮጵያን አትርፈን ቡድኑን ወደ ፈለገው ሲኦል ተረባርበን መሸኘት አለብንም ብለዋል።