አካባቢውን ከሰርጎ ገቦች ለመጠበቅ በዕዝ መምሪያ መሠረ ት የህዝባዊ ኃይል አደረጃጀቶችን በአግባቡና በየአከባቢው ያለውን ሰንከፎችን መንቀል በሚችል መልኩ መጠቀም እንዳለባቸው የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አክሊሉ አሳስበዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ  አውጅ ተግባራዊ ከሆነበት ጊዜ ጀምረው የተሰሩ ስራዎአች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና በየከሌው ያሉ ፍተሻና ጥበቃ በትኩረት ልሰራ ይገባል ብለዋል።

የዞኑ ህዝብ እስካሁን ድረስ ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ያደረገዉን ድጋፍና ፈጣን ምላሽ በዞኑ አስተዳደሪ ስም ዋና አስተዳዳሪው አመስግነዋል።

የተጀመረው ሀገር የማዳን ህልዉና ዘማቻና የአሸባሪዉን ህወሓት ቡድን እየተደመሰሰና እየተማረከ እንደሆነ ዋና አስተዳዳሪው ጠቅሰው አገራችን ኢትዮጵያ በቅርቡ ድል ታደርጋለችም ብለዋል።

አከባቢውን መጠበቅ የፖሊስና የምልሻ ስራ ብቻ ሳይሆን የሰው ሀይል ስምሪት በተቀመጠው አግባብ በመምሬት ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት መሠራት እንዳለበት የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነ አስታውቀዋል።

ከሀገራችን ህልውና የሚበልጥ ነገር የለም በሚል መንፈስ ሁሉም አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ ሀገራዊ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

ሀገር የማፍረስ እኩይ ተግባር ይዘው በማህበራዊ ሚዲያ የሚታትሩ አካላትና ቡድኖችን በጽናትና በቁርጠኝነት መመከት ይጠበቅብናል ብለዋል አቶ ዮሐንስ።

በውይይቱ የዞኑ አጠቃላይ አመራር፣ መድረኩ የወረዳ/ከተማ አስተዳዳሪዎች፣ የመንግስት ዋና ተጠሪዎችና የፀጥታ መዋቅር ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።