በትናንትናው ዕለት በዎላይታ ዞን በግቤ(ኦሞ) ሶስት ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ ተከትሎ በተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሀይቅ ወደ ስፍራው ለመዝናናት ካቀኑ 22 ተማሪዎች መካከል ሁለቱ በድንገት ሀይቅ ውስጥ መግባታቸውንና እስካሁን ከሀይቁ ውስጥ ባለመገኘታቸው የክንዶ ኮይሻ ወረዳ ፓሊስ በመፈለግ ላይ መሆኑን የወረዳው አዛዥ ሻለቃ ተስፋዬ ምስጋኑ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በስልክ ተናግረዋል።

አደጋው የደረሰው በትናንትናው ዕለት ሲሆን የዎላይታ ሊቃ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተና በማጠናቀቃቸው ወደ ሀይቁ ለመዝናናት አቅንተው ነበር።

አደጋው የደረሰበት የመጀመሪያው ተማሪ ከጀልባው ከወጣ በሁላ ብቻውን ለመዋኘት ሲሞክር ወደ ሀይቁ ከአቅም በላይ ሆነው መግባቱን የተመለከተው ሁለተኛው ተማሪ ጎዋደኛውን ለማዳን ገብቶ ለጉዳት መዳረጉንና እስካሁን ፖሊስ በተማሪዎቹ መጥፋት በባለሙያ የተደገፈ ፍለጋ ላይ መሆኑን ሻለቃ ተስፋዬ ለሚዲያችን ገልጸዋል።

ዝርዝርና የተጣራ መረጃ ሲደርስ ተጨማሪ መረጃዎችን እናደርሳለን በማለት አዛዡ ተናግረዋል።

ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1 በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።

Wolaita Times, 12/03/14 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹