በትናንትናው ዕለት ከቀኑ 8:00 ሰዓት አከባቢ በዎላይታ ዞን በግቤ(ኦሞ) ሶስት ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ ተከትሎ በተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሀይቅ ወደ ስፍራው ለመዝናናት ካቀኑ 22 የዎላይታ ሊቃ ተማሪዎች መካከል ሁለቱ በድንገት ሀይቅ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ በሀይቁ ውስጥ የክንዶ ኮይሻ ወረዳ ፓሊስ ባደረገው ርብርብ ተማሪዎችን በህይወት ማግኘት እንዳልተቻለ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ሻለቃ ተስፋዬ ምስጋኑ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከደቂቃዎች በፊት በስልክ ተናግረዋል።
አደጋው የደረሰው በትናንትናው ዕለት ሲሆን የዎላይታ ሊቃ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተና በማጠናቀቃቸው ወደ ሀይቁ ለመዝናናት አቅንተው ነበር ተብሏል።
አደጋው የደረሰበት የመጀመሪያው ተማሪ ከጀልባው ከወጣ በሁላ ብቻውን ለመዋኘት ሲሞክር ወደ ሀይቁ ከአቅም በላይ ሆነው መግባቱን የተመለከተው ሁለተኛው ተማሪ ጎዋደኛውን ለማዳን በመግባቱ እስካሁን ፖሊስ በተማሪዎቹ መጥፋት በባለሙያ የተደገፈ ፍለጋ በማድረግ የተማሪዎቹን አስከሬን ከአንድ ቀን ጥረት በሁዋላ ማግኘቱን ሻለቃ ተስፋዬ ለሚዲያችን አብራርተዋል።
ህብረተሰቡ ወደ ሀይቁ ሲሄድ የዋና ችሎታ ከለለው ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በመግለፅ ህይወታቸውን በድንገተኛ ሞት ያጡ ዘመድ ወዳጆች አዛዡ መፅናናትን ተመኝተዋል።
