በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የሚመሩት አርባ ምንጭ ከተማዎች በአራተኛ ሳምንት የሊጉ የመጀመሪያ መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማን 2 ለ 1 በዛሬው ዕለት ማሸነፍ ችሏል።
ሀቢብ ከማል እና ወርቅይታደስ አበበ አርባ ምንጭ ከተማን አሸናፊ ያደረገች ግብ ከመረብ አሳርፈዋል።
ፍፁም አለሙ የጣና ሞገደኞቹን ብቸኛ ግብ ማስቆጠር የቻለው ተጫዋች ሆኗል።
አርባ ምንጭ ከተማ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ከነበሩበት ስምንተኛ ደረጃ ሌሎች ቡድኖች እስኪጫወቱ በጊዜያዊነት ሶስተኛ ደረጃን መያዝ ችለዋል።
ወደ ሊጉ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ያደጉት አርባ ምንጮች በቀጣይ መርሐ ግብር አፄዎቹን የሚገጥሙ ይሆናል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 12/03/14 E.C , Sodo, Ethiopia
