በዎላይታ ሶዶ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ አራት ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱ ተገለፀ

በዛሬው ዕለት ከረፋዱ አምስት ሰዓት አከባቢ በሶዶ ከተማ ቆንቶ አባ ፋስካል የልጃገረዶች ትምህርት ቤት በር በተከሰተው ተሸከርካሪ አደጋ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማዋ ፖሊስ ፅ/ቤት የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ስራ ህደት አስተባባሪ እንስፐክቴር በላይ ባቡሎ ገልጸዋል።

አደጋው የተከሰተው ዛሬ ከረፋዱ 5:30 አከባቢ ሲሆን አደጋውን እንደተመለከትነው ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ኮዶ 3 51830ET የሆነ መኪና ተገልብጦ በሰው ህይወትና አካል ላይ ካደረሰው ጉዳት በተጨማሪ በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን አስተባባሪው አክለው ተናግረዋል።