በዎላይታ ዞን ወጣት አደረጃጀት አስተባባሪነት የዘማቾች ቤተሰብ ድጋፍና እንክብካቤ መርሃ ግብር “እኔም የዘማች ቤተሰብ አካል ነኝ” በሚል መሪ ቃል ዞናዊ መድረክ በቦዲቲ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በመርሃ ግብር ቦታ የተገኙ የደቡብ ክልል የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ኑሪዬ ሱሌ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ሉዓላዊነቷንና ነጻነቷን አስጠብቃ የኖረች ሀገር ስለሆነች በወራሪ ኃይልና በምዕራባዊያን ሴራ አትበተንም ብለዋል፡፡

የዜጎችን ክብር ለማስጠበቅ ጠቅላይ ሚኒሰተሩ ተከተሉኝ ብለው ወደ ግንባር መዘመታቸውን ጠቅሰው የሀገራችን ነጻነትን ለማስጠበቅ የሚያስችል በጠንካራ መሪ ጎን እንዲንቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሀገርን የማዳን ጥሪ ተቀብለው ወደ ግንባር የዘመቱ ጀግኖቻችን በየግንባሩ፣ በዱርና በገደሉ ለሚዋደቁ ቤተሰቦቻቸውን መደገፍና መንከባኬብ ከሁላችን እንደሚጠበቅ የዎላይታ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ ወ/ሮ እታገኘ ወ/ማርያም አስታውቀዋል፡፡

ወ/ሮ እታገኝ አክለውም የኢትዮጵያን መበተን ለሚፈልጉ አሸባሪዎች የሚመኙት ስዖል ለመሸኘት ወደ ግንባር የዘመቱ የዘማች ቤተሰቦቻቸው ትልቅ ኩራት ልሰማቸው ይገባልም ብለዋል፡፡

በም/ማዕረግ የቦዲቲ ከተማ ከንቲባ አቶ ታረቀኝ በደቾ በበኩላቸው የከተማ ህዝብ በጥቅት ቀናት ከ100 ኩ/ል በላይ እህልን ከ200 በላይ ዘማች ቤተሰቦች ድጋፍ መደረጉን ገልጸው ከተማ ህዝቡ ላደረገላቸው ድጋፍ ትልቅ ሞራልና ክብር አለኝ ብለዋል፡፡

ለዘማች ቤሰተቦች በሁሉም ቀበሊያት እህልን የማሰባሰብና የማሳ ማረስ መራሃ ግብር እየተካሄደ መሆኑንና ለዘማች ቤተሰቦች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም የዳሞት ወይዴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምራት ኩሣ አስታውቀዋል፡፡

የዎላይታ ዞን የወጣቶች ፕራዚዳንት አቶ ሚካኤል ዋዳ በበኩላቸው ለዘማች ቤተሰቦች ሀብት የማሰባሰብ፣ የደረሱ ሰብል የመሰባሰብ፤ የቤት እድሳት እና ለዘማቾች ደም ልገሳ በሁሉም መዋቅሮች እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ባለበቶቻቸውንና ልጃቸውን ወደ ጦር ግንባር የላኩት ዘማች ቤተሰቦች በልተን፣ ሰርተን ለማዋልና ለማደር ነጻነቷንና ሉዓላዊነቷን የጠበቀች ሀገር ያስፈልገናል ብለዋል፡፡

አያይዘውም በዚህም ታሪካዊ ሀገርን የማዳን ጥሪ ተቀብለው የዘመቱና በጀግናው ሀገር መከላከያ ጎን በመሆናቸው ኩራት እየተሰማን በቅርቡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ድል እንደሚታደርግም አንጠራጠርም ብለዋል።