በዞኑ የሴቶች አደረጃጀት ለመከላከያ ሰራዊት የሚሆን ሰንባች ስንቅ በማዘጋጀት ላይ ይገኛሉ።

የስንቅ ዝግጅቱ ለ5ኛ ዙሪ የሚከናወን ሲሆን በሶ፣ውሃ፣ስኳር፣ቆሎ እንደምገኝና በገንዘብ ስተመን ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ እንደምሆን ተገልጿል።

ስንቅ ዝግጅቱ ላይ የተገኙት የመንግሥት ረዳት ተጠሪና የገቢ አሰባሰብ ኮምቴ ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ ለምለም ከበደ እንደገለጹት የስንቅ ዝግጅቱ ለ5ኛ ዙሪ የሚከናወን መሆኑን በማብራራት በዚህ ዙሪ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ሰንቅ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን አብራርተዋል።

አሁን ላይ የስንቅ ዝግጅቱ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ደጀንነትን በሚያሳይ መልኩ በተለያዩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ህብረተሰብ ክፍሎች ወደ ግዳጅ ቀጠና የሚላክ ስንቅ በማዘጋጀት ላይ የሚገኙት መሆናቸውን በመግለፅ ምስጋናቸውን አቅርበው ስንቅ ዝግጅቱ የሚጠናከር መሆኑን ጠቁመዋል።

ሀላፊዋ በቀጣይነት ግንባር ድረስ በመሄድ ለመከላከያ ሰራዊታችን ስንቅ የማቀበል ድጋፉ እንደሚቀጥል አስታውቀው ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመቆም ሁላችንም የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

በስንቅ ዝግጅት ስራው የተሳተፉ እናቶች የሃገር መከላከያ ሠራዊት ለሃገር ሉዓላዊነት መከበር የማይተካ ህይወቱን እየሰጠ በመሆኑ አጋርነታችንን ለማሳየት ስንቅ እያዘጋጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ግንባር ድረስ በመሄድ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናችንን በተግባር ለማሳየት ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግሯል።