የዎላይታ ዲቻ ነገ የሚያሸንፉ ከሆነ ሊጉን በአንደኝነት መምራት ይጀምራሉ
⚽️ሰበታ ከተማ ከዎላይታ ዲቻ 🐝
ዘንድሮ ውጤት ተኮሩ ዎላይታ ድቻ
የየትኛውም ቡድን ደጋፊዎች ቡድናቸው አዘናንቶ ቢያሸንፍ ምርጫቸው ነው። ነገር ግን ከምንም በላይ አሸናፊ መሆኑ የበለጠ ዋጋ ይሰጠዋል። አዝናንቶ ማሸነፍ የሚለው አባባል በራሱ አከራካሪ ትርጓሚ ቢኖረውም ይበልጥ እዞራሱን ገልፆ ወይንም በአዎንታዊ አጨዋወት ማሸነፍ በሚለው ትርጓሚ እንኳን
ብንወስደው አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም በዎላይታ ድቻ እየገነቡት የሚገኘው ቡድን ግን እርሳቸውም እንደሚሉት በየትኛውም መንገድ ማሸነፍን ምርጫው
ያደረገ ሆኖ ሶከር ኢትዮጵያ ተመልከተናዋል።
ሊጉን በሽንፈት የጀመረው ወላይታ ድቻ በዚህኛው የጨዋታ ሳምንት ኢትዮጵያ ቡናን መርታቱን ተከትሎ ሦስተኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል። በሦስቱም ድል ባደረገባቸው ጨዋታዎች በአመዛኙ ወደ ራሱ ሜዳ ሰብሰብ ብሎ በመጫወት ተጋጣሚዎቹን በፈጣን የማጥቃት ሽግግሮች ለመጉዳት የሚጥር ቡድን እንደሆነ ተመልክተናል።
ይህም አጨዋወት ቡድኑ ባሸነፈባቸው የሀዋሳ ፣ አዳማ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታዎች በደንብ ቁልጭ ብሎ የተስተዋለ
እውነታ ነው። ዎላይታ ድቻ በ2006 የውድድር ዘመን ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ካደገበት ጊዜ አንስቶ ላለመሸነፍ ቅድሚያን በሚሰጥ አጨዋወት በመከላከሉ በጣም ጠጣር የሆነ እንዲሁም በመልሶ ማጥቃት የጨዋታ ውጤቶችን ለመወሰን የሚፈልግ ቡድን እንደሆነ ይታወቃል።
ቡድኑን እርግጥ እግርኳሳዊ ማንነት
ለማለት ቢከብድም ከዚህ የአጨዋወት መንገድ ወጣ ብሎ በተወሰነ መልኩ ኳስ ቁጥጥር ላይ ያተኮረ ቡድን ለመሆን በሞከራባቸው ወቅቶች ቡድኑ ምን ያህል በብዙ መንገድ እንደተቸገረ ተመልክተናል። አምናም አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ቡድን ተረክበው ቡድኑን ወደ መሰረታዊው ነገር እንዲመልስ በማስቻላቸው ከመውረድ ስጋት ተላቆ በሊጉ የተረጋጋ ስፍራን ይዞ ለማጠናቀቅ ችሏል።
ዘንድሮም በአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም እየተመራ የሚገኘው ድቻ የቡድኑን መሰረታዊ እሴቶችን በሚገባ ሜዳ ላይ እያስመለከተ በውጤት በማጀብ አሁን በሰንጠረዡ አናት ከፋሲል ከነማ ጋር በነጥብ በመስተካከል በሊጉ በሁለተኛ ደረጃ ለመቀመጥ በቅተዋል።
💚የጦና ንቦች ነገ የሚያሸንፉ ከሆነ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ ይቀመጣሉ!
⚽️ሰበታ ከተማ ከዎላይታ ዲቻ 🐝
ነገ ሰኞ ህዳር 20/2014
ምሽት 12 ሰዓት!
