የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለአምስት መምህራን የተባባሪና የረዳት ፕሮፌሰርነት ማህረግ ዕድገት ሰጠ።

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቷል።

ሴኔቱ ተወያይቶ ካጸደቃቸው ውሳኔዎች መካከል የመምህራን የተባባሪነት እና የረዳት ፕሮፌሰርነት የማህረግ እድገት ውሳኔ ዋንኛው ነው።

የዩኒቨርሲቲው ህገ-ደንብ በሚፈቅደው መሰረት የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ከተሰጣቸው 05 መምህራን መካላከል 4ቱ በረዳት ፕሮፌሰርነት ሲሆን አንዱ(01) ደግሞ በተባባሪ ፕሮፌሰርነት የማህረግ እድገት መሆኑ ተጠቁሟል።

የደረጃ ዕድገቱ ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ለተወጣጡ መምህራን የተሰጠ ሲሆን፤ ለማህረግ እድገት የተወዳደሩ መምህራን በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግር መስክ ያስመዘገቡት ውጤት በየደረጃው በሚገኙ የስራ እርከኖች ከማህደራቸው ተፈትሾ እንዲሁም ለዕድገቱ የተቀመጡ መመሪያዎችንና መስፈርቶችን ማሟላታቸው ተረጋግጦ የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የቀረበለትን የማህረግ እድገት ጥያቄ በሚገባ መርምሮ ለ 05 መምህራን የተባባሪነት እና የረዳት ፕሮፌሰርነት ማህረግ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

ለዩኒቨርሲቲው መምህራን የሚሰጠው የማህረግ እድገት በቀጣይ ጊዜያትም የተቋሙለ ህገ-ደንብ (ሌጅስሌሽን) በሚፈቅደው አግባብ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አሳውቀዋል።

ሴኔቱ ከመምህራን የተባባሪ እና የረዳት ፕሮፌሰርነት የማህረግ ዕድገት ውሳኔ በተጨማሪ በተማሪዎች ዓመታዊ የትምህርት ካላንደር፣ በግብርና ልዕቀት ማዕከል ፍኖተ ካርታ ሰነድ እንዲሁም በአዲሱ የሰራተኞች የዲሲፕሊን መተዳደሪያ ደንቦች ላይ ውይይት በማድረግ አቅጣጫ አስቀምጧል።

እንደ ዩንቨርስቲው ኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት ዘገባ በተባባሪነት እና በረዳት ፕሮፌሰርነት ደረጃ የማህረግ እድገት ያገኛችሁ ውድ የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር መልካም ምኞቱን ገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: