የዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ለሁሉም እስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1495ኛዉ የነቢዩ መሐመድ ልደት በዓል በሠላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
በዓሉ የሠላም፣ የፍቅርና የጤና እንዲሆን የተመኙት የከተማ አስተዳደሪ ከንቲባ አቶ ዘካሪያስ ታደሰ ሁሉም የእምነት ተከታዮች በዓሉን ሲያከብር የነበረውና በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚታወቅ አንድነትና መተሳሰብን በማጎልበት ሌላው ህብረተሰብም አስተማሪ በሆነ መልክ ሊያከብሩ ይገባል ብሏል።

ዎላይታ ሶዶ ከተማ ሁሉም ብሔርና እምነቶች ተከባብረውና ተቻችለው የሚኖሩባት ከተማ ነች ያሉት አቶ ዘካሪያስ ከዚህ በፊትም እንደሚናደረገዉ ሁሉ የከተማ አስተዳደርና ህብረተሰብ ለዚህ በዓል በሚያስፈልጉ አብሮነትም ይተባበራል ብሏል ።

አሁን እንደ ሀገራችን ብሎም እንደ ዓለም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እያደረሰ ያለዉን አስከፊነት ያነሱት ከንቲባው በዓሉ ሲከበር ግን የቫይረስ መከላከያ መንገዶችን በሚገባ ሊተገብር ይገባልም ብሏል ።

በዓሉን ሲናከብር አቅመ ደካሞችና ጠያቂ ያጡ ወገኖቻችን በመጠየቅ ሊሆን ይገባል ብለዉ ይህ ተግባር ግን ቀጣይነት እንዲኖረውም ከንቲባው ጥሪ አስተላልፈዋል ።

ሁሉም የሚሆነዉ ሠላምና መረጋጋት ሲኖር ነዉ ያሉት ከንቲባው የአከባቢውን ብሎም የከተማችን ሠላም ለማስጠበቅ ሁሉችንም ትኩረት ሊንሰጥ ይገባልም ብሏል።