#SHAEthiopia የዞን ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች መምሪያ ም/ል ኃላፊ ወ/ሮ ኢትዮጵያ አለሙ እንዲሁም ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ካምፎርድ ትምህርት ቤት ለሚማሩ ለ126 ተማሪዎች የትምህርት ቤት መልበሻ ዩኒፎርም፣ እስክርቢቶ፣ ለ45 ሴት ተማሪወች የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ እና 252 የሳሙና እና ቅባት ድጋፍ አድርጓል።
SHAPEthiopia በደቡብ ክልልና በሲዳማ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ በዳሞት ፑላሳ ወረዳ በሻንቶ ከተማ ከዛሬ 13 ዓመታት በፊት በእንጂነር ደሳለኝ ዳካ ተቋቁሞ አለምአቀፍና ሀገርቀፍ ለጋሾችን በማስተባበር በወረዳ ውስጥ ያሉ ወላጅ- አጥና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ህፃናትን በመርዳት የጀመረ ጅርጅት ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በወረዳው 126 ወላጅ- አጥና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ህፃናትን የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶች ማለትም የትምህርት ቤት ክፊያ፣ የትምህርት ቤት አለባሳት፣ ምግብ እና የህክምና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
በተጨማርም ይህ ድርጅት በወረዳው ውስጥ ህዝብ እንዲጠቀም የማህበረስብ ቤተ-መፅሐፍት (ላይብረሪ) ከሰባት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ከመገንባቱ ባለፈ ባሎቻቸውን በሞት ላጡ በቁጥር 200 የሚሆኑ እናቶችን በከብት እርባታ እና በአነስተኛ ንግድ ሥራ እንድሰማሩ አድርገዋል።
የሻንቶ ካምፎርድ ትምህርት ቤት በርካታ ማህበረሰብ አቀፍ ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ እና በወላይታ ዞን ከሊቃ ቀጥሎ በሀገር ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎችን እያፈራ የሚገኝ ት/ት ቤት መሆኑ ይገለፃል።
Reach