የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል ሰገን ጊዚያዊ ማሰልጠኛ ተቋም ለ7ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ሁለት ሺህ የሚጠጉ የልዩ ኃይል ሠራዊት አስመረቀ።
የክልሉ ፖሊስ ኮሌጅ ኃላፊ ምክትል ኮምሽነር አብርሃም ተርካሶ አሸባሪው ጁንታንና ተጋላቢው ኦኔግ ሸኔን ጀግናው ሠራዊታችን እያንበረከከ ባለበት ይህ ድል ዳግም መታየቱ ለተመራቂዎች ኩራት ነውና እንኳን ደስ አላችሁ ስሉ የደስታ መግለጫቸውን አሰምተዋል።
በሰገን የስልጠና ማዕከሉ የገቡ ወንድ 1,985 ሴት 200 በድምሩ 2,905 ሲሆን፤ 1,748 ወንዶችና 195 ሴቶች በድምሩ 1,943 ኮንስታብ የልዩ ኃይል ሠራዊቶች ዛሬ መመረቃቸውን ተናግረዋል።
በስልጠናው ወቅት 2 ሰልጣኞች በጤና እክል ምክንያት ወደ ቤተሰብ የተመለሱ ሲሆን 1,943 በብቁ አቅም ሰልጥነው መመረቃቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሌጅ ኃላፊ ምክትል ኮምሽነር አብርሃም ካልኪሶ አብራርተዋል።
በስልጠናው ካገኙት የኢላማ የተኩስ፣ የሽምቅ ውጊያ፣ የደፈጣ ውጊያ፣ ዲግ አፕ ፑል አፕ፣ ታዛ፣ አድማ ብተና፣ የኮማንዶ እና ሌሎች የቴክኒክ ብቃት ስልጠና ወስደው ብቁ ሆናችሁ ለምረቃ በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት የደቡብ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ ናቸው።
በአጭር ጊዜ ውስጥ የተለያዩ የአካል ብቃት ስልጠናዎችን በመውሰድ ለህዝባዊ አደራ ብሎም አገራዊ አለኝታነታ ብቁ መሆናቸውን የእለቱ የክብር እንግዳ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ ተናግረዋል።
በስልጠናው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ምልምል ኮንስታብሎች ሽልማት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ ተበርክቶላቸወቻል።

