የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ  ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ መስክ    ያሰለጠናቸው ከ 480 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል።

የኮሌጁ ችፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይረክተረ ዶክተር ሉቃስ ድንጋቶ ኮሌጁ ከህክምና አገልግሎት ጎን ለጎን በሙያው የተካኑ ተማሪዎችን በማሰልጠን በዛሬው ዕለት 4መቶ 56 ተማሪዎችን በመጀመሪያ ድግሪና 30 ተማሪዎችን  ደግሞ በሁለተኛ ድግሪ በአጠቃላይ 486 ተማሪዎችን  መመረቃቸውን ተናግረዋል።

የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ኦቶና ካምፋስ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 2ተኛ ዙር የተማሪዎች ምረቃ መረሃ ግብር ተማሪዎች በሰለጠኑበት የሙያ ያዳበሩትን ዕውቀት እንደትልቅ አቀም መጠቀም ሠላም የሰፈነባትና የበለፀገች ሀገር ለመጭው ትውልድ ለማስረከብ የበኩላቸውን እንድወጡ የዩንቨርስቲው ፕረዝዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ ጠይቀዋል።

የሰው ሀብት ልማት ለማደራጀት በተጀመረው ሥራ ለባለሙያዎች የትምህርት ዕድል በመስጠትም ባለሙያዎችን ከማብቃት አኳያ ዘረፋ ብዙ ተግባራትን ስያከናውን መቆየቱን አክለዋል።

ተመራቂ ተማሪዎችም በሀገር አደን ስራ በሙያ አሻራቸውን ማሳረፍ አለባቸው ስሉም ፕሮፌሰር ታከለ ተናግረዋል።

ተመራቂ ተማሪዎችንበሰለጠኑበት የሙያ መስክ ህዝቡን በታማኝነት ለማገልገል ቁርጠኛ መሆን እንዳለባቸው የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዩንቨርስቲው ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ከአክሊሉ ለማ ተናግረዋል።

በተለይ ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታን ለመመከት መንግስት በምፈልጋቸው በየትኛውም መስክ የሙያ ግዴታቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆን እንዳለባቸውም አቶ አክሊሉ አሳስበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: