የኃይለማሪያም ሮማን ፋውንዴሽን ቦርድ ሰብሳቢ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የኒጀር ቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት ኢሶፉ ሞሃመዶ የአፍሪካን ዋይልድላይፍ ፋውንዴሽን የግሎባል ትረስት ቦርድ አባል ሆነው መቀላቀላቸው ተገልጿል።

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በኃይለማሪያም ሮማን ፋውንዴሽን አማካይነት በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ዘርፍ ላይ በመሰማራት የላቀ ትኩረት እንዲሰጥ እና ኢትዮጵያም ከዘርፉ ተጠቃሚ እንድትሆን ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።

የአፍሪካ የዱር እንስሳት ጥበቃን እና አህጉራዊ ተጠቃሚነትን በተለየ አስውሎት በማቀንቀን ከፍተኛ ስራን እያከናወነ የሚገኘው የአፍሪካን ዋይልድላይፍ ፋውንዴሽን የዛሬ ስድሳ አመት የተመሰረተ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው። አቶ ኃይለማርያም በቦርድ አባልነት መቀላቀላቸው ኢትዮጵያ በዘርፉ የላቀ ትኩረት እንድታገኝ እንደሚረዳ ይታመናል።

በዘመናዊቷ አፍሪካ የዱር ሕይወት ሀብት ብልጽግና ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራው ይህ ተቋም በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ስራ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል ሲል ፋውንዴሽኑ በድረገጹ በዝርዝር አትቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: