የገና በዓል አከባበር በዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ


በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት (የገና በዓል) በድምቀት ተከበረ።

ድጋፍ ለሚሹ አካላት ከተማሪዎች የተሰበሰቡ አልባሳትን የማስተለፍና ማዕድ የማጋራት በጎ አድራጎት ተግባርም ተካሂዷል።

የሰላም አምባሳደር በሆነው ዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ትምህርት ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል።

ከ 8 ሺህ የሚበልጡ እና ከ1ኛ ዓመት በላይ የሆኑ መደበኛ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በሰላም ሲከታተሉ ቆይተዋል።

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርም የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት (የገና በዓል) ለማክበር ወደ ቤተሰብ ላልሄዱ ተማሪዎች በዓሉን በድምቀት እንዲያከብሩ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት አድርጓል።

ተማሪዎቹ በዛሬው እለት የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት (የገና በዓል) በድምቀት ያከበሩ ሲሆን፤ በበዓሉ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ፣ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ዴአ፣ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብርሃም ቦሻ፣ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ተመስገን ማርቆስ፣ የተማሪዎች ምክትል ዲን አቶ ዘገየ ጳውሎስ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በተማሪዎች ሕብረት አስተባባሪነት ከተማሪዎች የተሰበሰቡ አልባሳትን ድጋፍ ለሚሹ አካላት የማስተላለፍና ማዕድ የማጋራት በጎ አድራጎት ተግባር አካሂደዋል።

በመጨረሻም የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ ለመላው ኢትዮጵያን በተለይም ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የገና በዓል የደስታ፣ የሠላምና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: