ጃዋር መሐመድ፣ እስክንድር ነጋ ጨምረው ታስረው የነበሩ ግለሰቦች ከእስር ማምሻውን እየተለቀቁ መሆኑ ተገለፀ

እስክንድር ነጋን ጨምሮ ታስረው የነበሩ የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች እና አባላት ከእስር መለቀቃቸው ተገልጿል።

የፓርቲውን ሊቀመንበር እስክንድር ነጋን ጨምሮ ስንታየሁ ቸኮልን መሠል የፓርቲው አመራሮች ከእስር መፈታታቸውን ባልደራስ በማህበራዊ ገፁ አስታውቋል።

ጀዋር መሃመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎች የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ አመራሮች ይፈታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የአል ዐይን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል።

መንግስት የሀገር ሉአላዊነት ለማስቀጠልና ለመጠበቅ ሲባል የትኛውንም የሰላም መንገዶችን እጠቀማለሁ ማለቱ ይታወሳል።