በዎላይታ ዞን በኦፋ ወረዳ ባለፈው ሰኔ ወር በመንግሥት ስራ ከተቀጠሩት መካከል ከመቶ በላይ ሠራተኞች በሐሰት ማሰረጃ መቀጠራቸው ተነገረ።
በሐሰት ማሰረጃ የተቀጠሩ ሠራተኞች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደምወሰድም ወረዳው ገልጿል።
በዎላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ባለፈው ሰኔ ወር 2013 ዓ.ም ከተቀጠሩ 435 ሠራተኞች መከላከል የ134 ሠራተኞች ትምህርት ማሰረጃ ወደ ደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ተልኮ በተደረገው ማጣራት የዘጠኝ ሠራተኞች ብቻ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሴርትፊኬት ትክክለኛ ሲሆን 13 ሠራተኞች ደግሞ ከደረጃ 1- ደረጃ 3 ብቻ ትክክል ሆኖ ደረጃ 4 ግን ሐሰት እንደሆነና የቀሩት የ112 ሠራተኞች በሐሰት ማሰረጃ የተቀጠሩ መሆናቸውን የኦፋ ወረዳ ፐ/ሰ/ሰ/ል/ጽ/ ቤት ኃላፍ አቶ ማቴዎስ ጵልጦ ገልጸዋል።
አክለውም እነዚህን ለህግ እያቀረብን ጎን ለጎን የቀሩትን ሠራተኛ ማሰረጃ የማጣራት ሂደት የሚቀጥል መሆኑን አስረድተዋል።
በም/ማዕረግ የኦፋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተፈሪ ሌራ በጀት በሌለበት መቀጠራቸው ሳያንሰ በሐሰት ማሰረጃ መቀጠራቸው እጅግ ኃላፍነት የጎደለው ተግባር መሆኑን ገልፀው፣ በተደረገው ማጣራት በግምት በወር 313,488 ብር በላይ የሆነ የመንግስት ሀብት ከምዝበራ መትረፋን አስረድተዋል። በተጨማሪም እንደዚህ ዓይነቱ ህገ ወጥነት እንዳይደገም አጨብርባሪዎችን ወደ ህግ የማቅረብ ሥራ ይሠራል ብለዋል።
ያቀረቡት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ከኤጀንሲው ያልተሰጠ መሆኑን አረጋግጠናል ሲል ከኦፋ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ማህበራዊ ሚድያ ዘርፍ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
