ከዎላይታ ሶዶ-ሰላምበር-ሳውላ-ጅንካ የሚወስደው መንገድ በጊዜ ባለመጠናቀቁ ለማህበራዊና ለኢኮኖሚያዊ ችግር እየተጋለጡ መሆኑን የአከባቢው ነዋሪዎች ገለፁ።

መንገዱ ለአከባቢው ህዝቦች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ከፍ ያለ መሆኑን ተገንዝበው የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡም ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል።

ከዎላይታ ሶዶ ወደ ገሱባ፣ ሰላምበር፣ ጎፋ፣ ጂንካ የምወስደው የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ስራ በCRSG የመንገድ ተቋራጭ እየተሰራ የሚገኝ ስሆን ስራው በጊዜ ካለመጠናቀቁና መጓተቱን ተከትሎ ተሳፋሪዎችም ሆነ ባለንብረቶች ለአላስፈላጊ እንግልትና ወጪ እየተጋለጡ መሆኑን “የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ” ያነጋገራቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የመንገድ ሰራው እየተሰራ በጊዜ አለመጠናቀቁ ብቻ ሳይሆን በቂ የለውጥ መንገድ ሳይዘጋጅ መሰራቱ ለነጋዴው ማህበረሰብ ምርቱን በበቂ ሁኔታ ለገበያ ለማቅረብ አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱንም ተናግረዋል።

በተጨማሪም ከአከባቢው የህክምና አገልግሎት ለማገኝት ለሚጓዙ ታካሚዎች ሰሞኑን መጠነኛ ዝናብ ዘንቦ መንገዱ በመዘጋቱ ከፍ ያለ ጉዳት እየደረሰ በመሆኑ መንገዱ ለአከባቢው ህዝቦች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ከፍ ያለ መሆኑን ተገንዝበው የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡም “ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ” አስተያየት የሰጡ ነዋሪዎች ጠይቀዋል።

በደቡብ ኦሞ ዞን ጅንካ ከተማ እና የዎላይታ ዞን ሶዶ ከተማ የ216 ኪ.ሜ የቀጥታ ስምሪት የትራንስፓርት አገልግሎት ለበርካታ ዓመታት የህዝብ ጥያቄ የነበረው የቀጥታ ትራንስፓርት አገልግሎት ከዞኖች መምሪያ ኃላፍዎች፣ ትራንስፓርት ማህበራት ቦርድ አመራሮች እና ባለሙያዎች የትራንስፓርት መሥመር ጥናት ዙሪያ በተደረገው ውይይትና ስምምነት ተግባራዊ መሆኑ ይታወሳል።

በዚህም ከዎላይታ ሶዶ- አርባምንጭ- ኮንሶ- ጅንካ 354 ኪ.ሜ የነበረውን ከዎላይታ ሶዶ-ሰላምበር-ሻፌ-ቤቶ-ጅንካ 216 ኪ.ሜ በአጠቃላይ የ138 ኪ.ሜ በመቀነስ የጊዜ እና የገንዘብ ወጪ በማስቀረት ለህዝቦች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጠቀሜታው በተለይም የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማጠናከር ካለው ጉልህ ሚና አንፃር ከታህሳሥ 1/04/2012 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ቢሆንም ስራው በጊዜ ካለመጠናቀቁና መጓተቱን ተከትሎ ተሳፋሪዎችም ሆነ ባለንብረቶች ለአላስፈላጊ እንግልትና ወጪ እየተጋለጡ መሆኑን “የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ” ያነጋገራቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ቅሬታ አቅርቧል።

በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ከሚመለከታቸው አካላት እንዳገኝን ምላሹን በዝርዝር እናቀርባለን።

ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡Wolaita Timese/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channe /UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።

Wolaita Times, 11/05/14 E.C , Sodo, Ethiopia