የዎላይታ፣ ሀዲያ እና ከምባታና ጠንባሮ ዞኖች አጎራባች ህብረተሰብ ክፍሎችን የሚያገናኝ ድልድይና የህብረተሰቡ እሮሮ‼️
ይህ ሰሶቱ ዞኖች (የዎላይታ፣ ሀዲያ እና ከምባታና ጠንባሮ) ዞኖችና አጎራባች የሚገኙ ህብረተሰብ ክፍሎችን የሚያገናኝ ድልድይ ከሁለት አመት በፊት በጎርፍ በመወሰዱ በአከባቢው ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።
በምስሉ ከታች የምትመለክቱት ወንዝ በሃዲያ ዞን ምዕራብ ባዳዋቾ ወረዳ ዴዳ ቀበሌ በኩል ዎላይታ ዞን ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ከጋሜ ካቤቾ ቀበሌን የሚያዋስን ወንዝ ስሆን ከክረምት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ከረዥም ዓመት ጀምሮ ሁለቱ ወረዳ ሕዝቦች ይጠቀሙበት የነበረው የእንጨት ድልድይ በጎርፍ ውኃ በመቋረጡ በኢኮኖሚዊ፣ በማህበራዊ፣ በህዝብ ግንኝነት፣ በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ ከነዋሪዎቹ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከዚህ የተነሳ በፊት ከዎላይታ ቦዲት፣ ሻንቶ፣ ዋሴዶ፣ ሌራ አካባቢ እስከ ከምባታ ዞን ዱራሜ፣ ሽንሽቾ እና ሃዲያ ዞን ስቄ ዳናማ እና ዋዳ ገበያ የቁም እንስሳ፣ ቡና፣ ፍራፍሬ እና ለሌሎች ግብይት ስገበይ የነበረው ግብይት መቋረጡን አረጋግጠዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በዎላይታ ዞን አጎራባች በሆነው ሃዲያ ምዕራብ ባዳዋቾ ወረዳ፣ ከምባታ ዞን በትምህርት በጤና እና በግብርና ሥራና በማህበራዊ ትስስር አሉታዊ ተዕጽኖ እያደረሰ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
የዚህ ወንዝ ችግር በቃላት ከሚንገልጻው በላይ ነውና ደግሞ ይህ ድልድይ ቢሠራ ጥቅሙ ለአከባቢው ህዝቦች እጂግ የላቀ ይሆናል ስሉም የአከባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
የሚመለከተው የሁለቱ የዞንና የወረዳ የመንግሥት አካላት እንዲሁም በሁለቱ አካባቢ የሚገኙ ህብረተሰብ አካላት አስተባብረው ለመፍትሔው እንዲረባረቡ ከስፍራው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በድጋሚ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
በጉዳዩ ዙሪያ ባለድርሻ አካላትን ጠይቀን ምላሽ እንዳገኘን የምናደርስ መሆኑን እንገልፃለን።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1 በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 28/05/14 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹

